ደህንነትዎን መስመር ላይ ይበልጥ የተጠበቀ እንዲያደርጉ የሚያግዙ ጠቃሚ ምክሮች

ይበልጥ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን እንዲፈጥሩ፣ መሣሪያዎችዎን እንዲጠብቁ፣ የማስገር ሙከራዎችን ለመከላከል እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በይነመረቡን እንዲያስሱ አንዳንድ ፈጣን ጠቃሚ ምክሮችን እና ምርጥ ልምዶችን አሰባስበናል።

የመለያዎን ደህንነት ያጠናክሩት

 • የደህንነት ፍተሻውን ያድርጉ

  የእርስዎን የGoogle መለያ ጥበቃ ለማድረግ አንዱ ቀላል ዘዴ የደህንነት ፍተሻን ማከናወን ነው። የእርስዎን የGoogle መለያ ደህንነት ይበልጥ ማጠናከር እንዲችሉ እርስዎን ለማገዝ እንዲቻል ለእርስዎ ግላዊነት የተላበሱ እና ሊከናወኑ የሚችሉ የደህንነት ጠቃሚ ምክሮችን ለመስጠት ይህን ደረጃ በደረጃ የሚያስረዳ መሣሪያ ገንብተናል።

 • ጠንካራ የይለፍ ቃላትን ይፍጠሩ

  ጠንካራ፣ ልዩ የይለፍ ቃል መፍጠር የእርስዎን መስመር ላይ መለያዎች ለመጠበቅ መውሰድ ከሚችሏቸው ወሳኝ እርምጃዎች መካከል አንዱ ነው። እርስዎ በማይረሷቸው ነገር ግን ለሌሎች ለመገመት አስቸጋሪ የሆኑ ተከታታይ ቃላትን በመጠቀም ይህን ማድረግ ይችላሉ። ወይም ደግም አንድ ረጅም ዓረፍተ ነገር ይውሰዱና የእያንዳንዱን ቃል የመጀመሪያው ፊደል ወስደው አንድ ይለፍ ቃል ይገንቡ። ይበልጥ ጠንካራ ለማድረግ የስምንት ቁምፊ ርዝመት ያለው ያድርጉት፣ ምክንያቱም የይለፍ ቃልዎ በረዘመ ቁጥር ይበልጥ ጠንካራ ይሆናል።

  ለደህንነት ጥያቄዎች መልሶችን እንዲፈጥሩ ከተጠየቁ ለመገመት ይበልጥ አስቸጋሪ ለማድረግ የውሸት መልሶችን ይጠቀሙ።

 • ለእያንዳንዱ መለያ ልዩ የይለፍ ቃላትን ይጠቀሙ

  ተመሳሳዩን የይለፍ ቃል ተጠቅመው እንደ የእርስዎ Google መለያ፣ ማኅበራዊ ሚዲያ መገለጫዎች እና የችርቻሮ ድር ጣቢያዎች ወዳሉ በርካታ መለያዎች መግባት የደህንነት አደጋዎን ይጨምረዋል። ልክ የእርስዎን ቤት፣ መኪና እና ቢሮ ለመቆለፍ ተመሳሳዩን ቁልፍ የመጠቀም ያህል ነው – የሆነ ሰው የአንዱን መዳረሻ ካገኘ ሁሉም ሊሰረቁ ይችላሉ። ለእያንዳንዱ መለያ ልዩ የሆነ የይለፍ ቃል መፍጠር ይህን አደጋ ይቀንሳል እንዲሁም የእርስዎን መለያዎች ይበልጥ ደህንነታቸው የተጠበቁ እንዲሆኑ ያደርጋል።

 • በርካታ ይለፍ ቃላትን ዱካ ይከታተሉ

  የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ፣ በGoogle መለያዎ ውስጥ ያለው አይነት፣ በጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ የሚጠቀሙባቸውን የይለፍ ቃላት እንዲጠብቁ እና እንዲከታተሉ ያግዘዎታል የGoogle ይለፍ ቃል አስተዳዳሪ እርስዎን በጥንቃቄ እና በቀላሉ ወደ መለያ እንዲያስገባዎት የተቀመጡ ይለፍ ቃላትዎን ይጠቀማል

 • በባለ2-ደረጃ ማረጋገጫ አማካኝነት ከሰርጎ-ገቦች ይከላከሉ

  ባለ2-ደረጃ ማረጋገጫ ወደ መለያዎ ለመግባት በተጠቃሚ ስምዎ እና ይለፍ ቃልዎ ላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲጠቀሙ በማድረግ መዳረሻ የማይገባቸውን ሰዎች ይከለክላል። ለምሳሌ፣ Google ጋር ይሄ ከGoogle አረጋጋጭ መተግበሪያው በሚመነጭ ባለስድስት አኃዝ ኮድ ወይም ከታመነ መሣሪያ የመጣን መግባት ለመቀበል በGoogle መተግበሪያዎ ውስጥ ባለ ጥያቄ አማካኝነት ይሄ ይቻላል።

  ከማስገር ተጨማሪ ጥበቃን ለማግኘት በኮምፒውተርዎ ዩኤስቢ ወደብ ላይ የሚሰካ ወይም የቅርብ ርቀት ግንኙነት ወይም ብሉቱዝን በመግዛት ከተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ጋር የሚገናኝ አካላዊ የደህንነት ቁልፍ መጠቀም ይችላሉ። የመብት ተሟጋቾች፣ ጋዜጠኞች ወይም የፖለቲካ ዘመቻ ቡድኖችን ጨምሮ – በከፍተኛ ደረጃ ዒላማ ለሚደረጉ ጥቃቶች ተጋላጭ የመሆን ስጋት ያላቸው ማናቸውም ሰዎች – የላቀ ጥበቃ ፕሮግራም የGoogleን በጣም ጠንካራውን መከላከያ እንደ የባለ2-ደረጃ ማረጋገጨ ብቸኛ ዓይነት አካላዊ የደህንነት ጥበቃ ቁልፍን መጠቀምን ያቀርባል።

መሣሪያዎችዎን ይጠብቁ

 • ሶፍትዌርን እንደተዘመነ ያቆዩ

  ራስዎን ከደህንነት ተጋላጭነቶችን ለመጠበቅ ሁልጊዜ በመላው የእርስዎ ድር አሳሽ፣ ስርዓተ-ክወና፣ ተሰኪዎች እና የሰነድ አርታዒያን ላይ የተዘመነ ሶፍትዌር ይጠቀሙ። ሶፍትዌርዎን እንዲያዘምኑ ማሳወቂያዎች ሲደርሱዎት በተቻለዎት ፍጥነት ያድርጉት።

  ሁልጊዜ የሚገኙትን የቅርብ ጊዜ ስሪት እየተጠቀሙ መሆንዎ ለማረጋገጥ በመደበኝነት የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ይገምግሙ። የChrome አሳሽን ጨምሮ አንዳንድ አገልግሎቶች ራሳቸውን በራስ-ሰር ያዘምናሉ።

 • ሊጎዱ የሚችሉ መተግበሪያዎች ከስልክዎ ያርቋቸው

  ሁልጊዜ የሞባይል መተግበሪያዎችዎን ከሚያምኑት ምንጭ ያውርዱ። የAndroid መሣሪያዎች ደህንነት እንደተጠበቁ እንዲቆዩ ለማገዝ Google Play ጥቃት መከላከያ መተግበሪያዎችን ከGoogle Play መደብር ከማውረድዎ በፊት የጥንቃቄ ፍተሻ ያካሂድባቸዋል፣ እና መሣሪያዎ ከሌሎች ምንጮች የመጡ ሊጎዱ የሚችሉ መተግበሪያዎች ካሉ በየጊዜው ይፈትሻል።

  የእርስዎን ውሂብ ደህንነቱ እንደተጠበቀ ለማቆየት፦

  • መተግበሪያዎችዎን ይገምግሙ፣ እና የማይጠቀሙባቸውን ይሰርዙ።
  • የመተግበሪያ መደብር ቅንብሮችዎን ይጎብኙና ራስ-ዝማኔዎችን ያንቁ።
  • እንደ የእርስዎ አካባቢ እና ፎቶዎች ያለ ሚስጥራዊነት ያለው የውሂብ መዳረሻ ለሚያምኗቸው መተግበሪያዎች ብቻ ይስጡ።
 • የማያ ገጽ ቁልፍ ይጠቀሙ

  የእርስዎን ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ጡባዊ ወይም ስልክ በማይጠቀሙበት ጊዜ ሌሎች ወደ የእርስዎ መሣሪያ እንዳይገቡ ለመከላከል ማያ ገጽዎን ይቆልፉት። ለተጨማሪ ደህንነት ሲባል መሣሪያዎ ሲያሸልብ በራስ-ሰር እንዲቆልፍ ያቀናብሩት።

 • ስልክዎ ከጠፋብዎ ይቆልፉት

  የእርስዎ ስልክ የጠፋ ወይም የተሰረቀ እንደሆነ ውሂብዎን በጥቂት ፈጣን ደረጃዎች ለመጠበቅ የእርስዊ Google መለያ ን ይጎብኙና «ስልክዎን ያግኙ»ን ይምረጡ። የAndroid ወይም የiOS መሣሪያ ይሁን ያለዎት ሌላ ማንም ሰው ስልክዎን እንዳይጠቀም እና የግል መረጃዎን እንዳይደርስ ለማድረግ ስልክዎን በርቀት ማግኘትና መቆለፍ ይችላሉ።

ከማስገር ሙከራዎች ይከላከሉ

 • ሁልጊዜ አጠራጣሪ ዩአርኤሎችን ወይም አገናኞችን ያረጋግጡ

  ማስገር እንደ የይለፍ ቃል ያለ ወሳኝ የግል መረጃ አሳልፈው እንዲሰጡ የሚደረግ የማታለል ሙከራ ነው። ብዙ መልክ ሊይዝ ይችላል፣ ስለዚህ እንዴት አጠራጣሪ ኢሜይሎችን እና ድር ጣቢያዎችን መለየት እንደሚቻል ማወቅ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ሰርጎ-ገብ ሕጋዊ የሚመስል የመግቢያ ገጽ ሊፈጥር ይችላል፣ ነገር ግን የሐሰት ነው፣ እና አንዴ የይለፍ ቃልዎ ከታወቀ በኋላ ሰርጎ-ገቡ መለያዎን ሊደርስ ወይም ማሽንዎን ሊበክል ይችላል።

  በአስጋሪ ኢሜይል ላለመጠለፍ፦

  • አጠያያቂ በሆኑ አገናኞች ላይ በጭራሽ ጠቅ አያድርጉ። ሁልጊዜ ውሂብዎን የሚያስገቡት ህጋዊ ወደሆነ ድር ጣቢያ ወይም መተግበሪያ መሆኑን ለማረጋገጥ ዩአርኤሉን ደጋግመው ይፈትሹ።
  • ማናቸውንም መረጃ ከማስገባትዎ በፊት የጣቢያው ዩአርኤል በ«https» የሚጀምር መሆኑን ያረጋግጡ።
 • ከአስመሳዮች ይጠንቀቁ

  የሆነ የሚያውቁት አንድ ሰው ኢሜይል ቢልክልዎ፣ ነገር ግን መልዕክቱ ግራ የሚያጋባ ነገር ከሆነ መለያቸው ተጠልፎ ሊሆን ይችላል። ኢሜይሉ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ እስኪችሉ ድረስ ለመልዕክቱ ምላሽ አይስጡ ወይም ማናቸውንም አገናኞች ጠቅ አያድርጉ።

  እንደሚከተሉት ያሉትን ነገሮችን ይመልከቱ፦

  • የገንዘብ አስቸኳይ ጥያቄዎች
  • በሌላ አገር ውስጥ ሆኖ መሄጃ መድረሻ ጠፋኝ የሚል ግለሰብ
  • ስልካቸው ተሰረቀብን እና ጥሪ ሊደረግለት አይችልም የሚሉ ግለሰብ
 • የግል መረጃን የሚጠይቁ ይጠራጠሩ

  እንደ የይለፍ ቃላት፣ የባንክ ሒሳብ እና የክሬዲት ካርድ ቁጥሮች ወይም እንዲያውም የልደት ቀንዎን ለሚጠይቁ ለአጠራጣሪ ኢሜይሎች፣ ፈጣን መልዕክቶች ወይም ብቅ-ባይ መስኮቶች ምላሽ አይስጡ። መልዕክቱ እንደ የእርስዎ ባንክ ካለ የሚያምኑት ጣቢያ የመጣ ቢሆንም እንኳ በጭራሽ አገናኙን ጠቅ አያድርጉ ወይም የምላሽ መልዕክት አይላኩ። በቀጥታ ወደ ድር ጣቢያቸው ወይም መተግበሪያቸው ሄዶ መግባቱ ይሻላል።

  ያስታውሱ፣ ሕጋዊ ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች የይለፍ ቃላትን ወይም የፋይናንስ መረጃን በኢሜይል በኩል እንዲልኩ የሚጠይቁ መልዕክቶችን አይልኩም።

 • ከኢሜይል ማጭበርበሪያዎች፣ የሐሰት ሽልማቶች እና ስጦታዎች ይጠንቀቁ

  ከማያውቋቸው ሰዎች የመጡ መልዕክቶች ሁልጊዜ አጠራጣሪ ናቸው፣ በተለይ እውነት በማይመስል መልኩ ጥሩ ከመሰሉ — ለምሳሌ የሆነ ነገር እንዳሸነፉ ማስታወቅ፣ አንድ የዳሰሳ ጥናት በማጠናቀቅ ሽልማት መውሰድ ወይም ገንዘብ የሚሠሩባቸውን ፈጣን መንገዶች ማስተዋወቅ። አጠራጣሪ አገናኞችን በጭራሽ ጠቅ አያድርጉ፣ እና አጠያያቂ በሆኑ ቅጾችና የዳሰሳ ጥናቶች ላይ በጭራሽ የግል መረጃ አያስገቡ።

 • ፋይሎችን ከማውረድዎ በፊት ደጋግመው ይፈትሿቸው

  አንዳንድ ረቀቅ ያሉ የማስገር ጥቃቶች በተበከሉ የሰነዶች እና ፒዲኤፍ ዓባሪዎች በኩል ሊከሰቱ ይችላሉ። አንድ አጠራጣሪ ዓባሪ ካጋጠመዎት ለመክፈትና መሣሪያዎን የማስበከል ዕድሉን ለመቀነስ Chrome ወይም Google Driveን ይጠቀሙ። ቫይረስ ካገኘን ማስጠንቀቂያ እናሳይዎታለን።

ደህንነታቸው በተጠበቁ አውታረ መረቦች እና ግንኙነቶች ላይ ማሰስ

 • ደህንነታቸው የተጠበቁ አውታረ መረቦችን ይጠቀሙ

  ይፋዊ ወይም ነጻ Wi-Fi መጠቀም ላይ ይጠንቀቁ፣ የይለፍ ቃል የሚጠይቁ ቢሆኑም እንኳ። እነዚህ አውታረመረቦች ያልተመሣጠሩ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ ከአንድ ይፋዊ አውታረ መረብ ጋር ሲገናኙ በአካባቢው ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው እንደ የሚጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች እና በጣቢያዎች ላይ የሚተይቡት መረጃ ያለ የበይነመረብ እንቅስቃሴዎን መከታተል ይችላል። ይፋዊ ወይም ነጻ Wi-Fi ብቸኛው አማራጭዎ ከሆነ የChrome አሳሹ ጣቢያው ደህንነቱ የተጠበቀ ከሆነ በአድራሻ አሞሌው ላይ ያሳውቀዎታል። በቤት ውስጥ እንኳ ሳይቀር የእርስዎ Wi-Fi አውታረ መረብ እንደተመሣጠረ በማረጋገጥ እና ጠንካራ የይለፍ ቃል በማቀናበር የእርስዎን የአሰሳ እንቅስቃሴ ግላዊነት እና ደህንነት ይጠብቁ።

 • ምሥጢራዊነት ያለው መረጃ ከማስገባትዎ በፊት ደህንነታቸው የተጠበቁ ግንኙነቶችን ይፈልጉ

  ድሩን ሲያስሱ – እና በተለይ እንደ የይለፍ ቃል ወይም የክሬዲት ካርድ ቁጥር ያለ ምሥጢራዊነት ያለው መረጃን የማስገባት ሐሳብ ካለዎት – ከሚጎበኟቸው ጣቢያዎች ጋር ያለው የግንኙነት ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጡ። ደህንነቱ የተጠበቀ ዩአርኤል ከሆነ የChrome አሳሹ በዩአርኤል መስኩ ላይ ግራጫ፣ ሙሉ በሙሉ የተቆለፈ አዶን ያሳያል። HTTPS የእርስዎን አሳሽ ወይም መተግበሪያ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ከሚጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች ጋር በማገናኘት የእርስዎን አሰሳ በጥንቃቄ ይይዛል።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።