የእርስዎን የግል መረጃ ለማንም አንሸጥም

በGoogle ምርቶች ውስጥ፣ በአጋር ድር ጣቢያዎች ላይ እና በሞባይል መተግበሪያዎች ውስጥ ተገቢ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ ውሂብ እንጠቀማለን። እነዚህ ማስታወቂያዎች የእኛን አገልግሎቶች የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ ለማቅረብ እና ለሁሉም ሰው በነጻ እንድናቀርባቸው እንድንችል የሚያግዙ ሲሆኑ የግል መረጃዎ ለሽያጭ አይቀርብም። እርስዎ እንዲሁም የሚመለከቷቸውን ማስታወቂያዎች በተሻለ ሁኔታ መቆጣጠር እንዲችሉ ኃይለኛ የማስታወቂያ ቅንብሮችን እናቀርብልዎታለን።

የGoogle ማስታወቂያዎች እንዴት እንደሚሰሩ

 • ማስታወቂያዎች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ ለማድረግ ውሂብን እንጠቀማለን።

  ውሂቡን የምንጠቀምበት አገልግሎቶቻችን ይበልጥ ጠቃሚ እና ተገቢ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ነው፣ ይህም አገልግሎቶቻችን ለሁሉም ሰው ነጻ እንዲሆን ያግዛል። የእርስዎን ማንነት ለማስታወቂያ ሰሪዎች ወይም ለሌሎች ሶተኛ ወገኖች ሳናሳውቅ የእርስዎን ፍለጋዎች እና አካባቢ፣ የተጠቀሙባቸው ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች፣ የተመለከቷቸው ቪዲዮዎች እና ማስታወቂያዎች እና እንደ የእርስዎ የዕድሜ ክልል እና ጾታ ያለ ለእኛ የሰጡን መሠረታዊ መረጃ ልንጠቀም እንችላለን።

  በእርስዎ የማስታወቂያ ቅንብሮች የሚወሰን ሆኖ እና በመለያ ከገቡ ይህ ውሂብ እርስዎ በመላ መሣሪያዎችዎ እና ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከእኛ ጋር አጋር በሚሆኑ ጣቢያዎች ላይ የሚመለከቷቸውን ማስታወቂያዎች ይለያል። ስለዚህ ስራ ላይ በኮምፒውተርዎ ላይ አንድ የጉዞ ድር ጣቢያን ከጎበኙ በኋላ ማታ ላይ በስልክዎ ላይ በGoogle የቀረቡ ወደ ፓሪስ ስለሚወስዱ የአየር በረራዎች ማስታወቂያዎች ሊያዩ ይችላሉ።

 • ማስታወቂያዎችን ባስቀመጡ ማስታወቂያ ሰሪዎች እንከፈላለን

  [በማስታወቂያ ላይ እንዴት ገንዘብ እንደምናገኝ] (https://howwemakemoney.withgoogle.com/) ላይ ግልጽ መሆን አንፈልጋለን፣ በሁለቱም በአገልግሎቶቻችን እና ከእኛ ጋር አጋር በሆኑ ጣቢያዎችና መተግበሪያዎች ላይ። ለአንዳንድ የማስታወቂያዎች አይነቶች ማስታወቂያ ሰሪዎች እነዚህ ማስታወቂያዎች ለተቀመጡበት ብቻ የሚከፍሉን ሲሆን ለሌሎች አይነቶች እነዚያ ማስታወቂያዎች ባላቸው ትክክለኛ አፈጻጸም ላይ ተመስርተው ነው የሚከፍሉን። ይህ የሆነ ሰው አንድን ማስታወቂያ በተመለከተ ወይም መታ ባደረገ ቁጥር ወይም እንደ አንድ መተግበሪያ ማውረድ ወይም የጥያቄ ቅጽን መሙላት ያለ ድርጊት ባከናወነ ቁጥር ሊያካትት ይችላል።

 • የማስታወቂያ ሰሪዎች ዘመቻዎች እንዴት እንደሠራላቸው እንነግራቸዋለን

  ማስታወቂያ ሰሪዎች ስለማስታወቂያዎቻቸው አፈጻጸም መረጃ እንሰጣቸዋለን፣ ነገር ግን ይህን የምናደርገው ምንም የግል መረጃዎን ሳናሳይ ነው። ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን በማሳየት ሂደት ላይ ባለው እያንዳንዱ ነጥብ ላይ የእርስዎን የግል መረጃ እንደተጠበቀ እና የግል ጉዳይ እንደሆነ እናቆየዋለን።

በGoogle ማስታወቂያ ተሞክሮዎ ላይ ቁጥጥር ለእርስዎ መስጠት

 • Google ለእርስዎ ግላውነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ምን መረጃ እንደሚጠቀም ይቆጣጠሩ

  በማስታወቂያ ቅንብሮች ውስጥ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ግላዊነት ለማላበስ የምንጠቀምበት ውሂብ መቆጣጠር ቀላል እናደርግልዎታለን። ይህ ወደ የGoogle መለያዎ ያከሉት መረጃ፣ በእንቅስቃሴዎ አማካኝነት ስለፍላጎቶችዎ ያደረግናቸው ግምቶች እና ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከእኛ ጋር አጋር ከሆኑ ሌሎች ማስታወቂያ ሰሪዎች ጋር ያሉ መስተጋብሮችን ያካትታል።

  የእርስዎ እንቅስቃሴ ምን እንደምናሳየዎት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል፣ ነገር ግን እርስዎ ነዎት ሁልጊዜ ተቆጣጣሪ የሆኑት። ለምሳሌ፣ በYouTube ላይ የቅርብ ጊዜ ግጥሚያ ድምቀቶችን ስለተመለከቱ ወይም በGoogle ፍለጋ ላይ «ከእኔ አጠገብ ያሉ የእግር ኳስ ሜዳዎች» ስለፈለጉ የእግር ኳስ አድናቂ እንደሆኑ ልናስብ እንችላለን። እና በአንድ የአጋር ማስታወቂያ ሰሪ ድር ጣቢያ ላይ የተወሰነ ጊዜ ከወሰዱ በዚያ ጉብኝት ላይ ተመስርተን ማስታወቂያቆችን ልንጠቁም እንችላለን።

  ማስታወቂያን ግላዊነት ማላበስ ሲበራ ማንኛውም መረጃ መምረጥ – ዕድሜ እና ጾታ፣ የተገመተ ፍላጎት ወይም ከዚህ ቀደም ከአንድ ማስታወቂያ ሰሪ ጋር የነበረ መስተጋብር – ለምን ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ ተጨማሪ ማወቅ ወይም ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን በአጠቃላይ ማቦዘን ይችላሉ። አሁንም ማስታወቂያዎችን ይመለከታሉ፣ ነገር ግን ተገቢነታቸው ያነሰ የመሆኑ ዕድል ከፍ ይላል።

 • ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ምን ውሂብ እንደምንጠቀም ይመልከቱ

  ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት የምንጠቀመውን ውሂብ እንዲያውቁ ማገዝ እንፈልጋለን። «ለምን ይህ ማስታወቂያ» አንድን ማስታወቂያ ለምን እየተመለከቱ እንዳሉ እንዲረዱ የሚያግዝዎት ባህሪ ነው። ለምሳሌ፣ ካሜራዎችን ስለፈለጉ፣ የፎቶግራፍ አነሳስ ጥበብ ድርጣቢያዎችን ስለጎበኙ፣ ወይም ከዚህ ቀደም በካሜራዎች ማስታወቂያዎች ላይ ጠቅ ስላደረጉ ያንን የካሜራ ማስታወቂያ እያዩ ያሉ ሊሆን ይችላል። ወይም የአንድ ምግብ ቤት ማስታወቂያን ከተመለከቱ ይህ የሆነው ባሉበት አካባቢ ምክንያት እንደሆነ ሊያውቁ ይችላሉ። እንዲህ ያለው የውሂብ ዓይነት እርስዎ ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኟቸው ስለሚችሏቸው ነገሮች ያሉ ማስታወቂያ እንድናሳይ ያግዘናል። ነገር ግን ያስታውሱ፣ ይህን የግል መረጃ በጭራሽ ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች አንጋራውም።

  በእኛ እንደ ፍለጋ፣ YouTube፣ Gmail፣ Play፣ እና ግብይት የመሳሰሉ አገልግሎቶች ላይ ባለ የመረጃ አዶ በኩል ይህን ባህሪ ሊደርሱበት ይችላሉ። የእኛን አገልግሎቶች በሚጠቀሙ የአጋር ጣቢያዎች ላይ ወይም መተግበሪያዎች ውስጥ ለአብዛኛዎቹ ማስታወቂያዎች፣ «ለምን ይህ ማስታወቂያ»ን በተመሳሳይ አዶ በኩል ሊደርሱበት ይችላሉ።

 • ማየት የማይፈልጓቸውን ማስታወቂያዎች ያስወግዱ

  በአጋሮቻችን ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች በኩል የምናሳያቸውን ማስታወቂያዎች ልክ ሲመለከቷቸው ሊያስወገዷቸው ይችላሉ። በማስታወቂያው ጥግ ላይ ያለውን X በመምረጥ ከአሁን በኋላ ተገቢ ሆነው የማያገኟቸውን ማስታወቂያዎች ማስወገድ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ አዲስ መኪና ለመግዛት እየፈለጉ ሳሉ የመኪና ማስታወቂያዎች ጠቃሚ ሆነው ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን አንዴ አዲስ መኪና ገዝተው በደስታ መንዳት ከጀመሩ በኋላ ስለገዙት መኪና ማስታወቂያ ዳግመኛ ማየት ላይፈልጉ ይችላሉ።

  ወደ መለያ ከገቡና በእርስዎ የማስታወቂያዎች ቅንብሮች ላይ የሚወሰን ሆኖ ይህ ቁጥጥር ከእኛ አጋር በፈጠሩ ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ እርስዎ በመለያ በገቡባቸው መሣሪያዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል። እንዲሁም በChrome እና በአብዛኛዎቹ ሌሎች አሳሾች ውስጥ ብቅ-ባይ ማስታወቂያዎችን የማጥፋት አማራጭ አለዎት።

 • ከተወሰኑ ማስታወቂያ ሰሪዎች የሚመጡ ማስታወቂያዎች ያጥፉ

  በማስታወቂያዎች ተሞክሮዎ ላይ እርስዎ ቁጥጥር አለዎት፣ በሁለቱም በGoogle ምርቶች እና በመላ በይነመረቡ ላይ። ማስታወቂያ ሰሪዎች አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ጣቢያዎቻቸውን ሲጎበኙ እና ተመልሰው መጥተው እንዲጎበኙ ለማበረታታት ማስታወቂያዎችን ሊያሳዩዎት ይችላሉ – ለምሳሌ ቀደም ብለው ለገበያ ሲመለከቷቸው የነበሯቸው የጫማዎች ማስታወቂያ ሲመለከቱ። ከእንግዲህ በማንኛውም ምክንያት እነዚህን ማየት ካልፈለጉ በፍለጋ፣ YouTube እና Gmail እርስዎን በመላ የGoogle ንብረቶቻችን ላይ እርስዎን ከሚከተለ ማስታወቂያ ሰሪ የሚመጡ እነዚህን ማስታወቂያዎች ማጥፋት ይችላሉ። ይህ ቅንብር እርስዎ በበይነመረብ እና ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከእኛ ጋር አጋር በሚሆኑ ጣቢያዎችና መተግበሪያዎች ላይ በሚመለከቷቸው ማስታወቂያዎች ላይ ይተገበራል።

  በማስታወቂያ ቅንብሮችዎ ውስጥ ገብተው ሳለ እንዲሁም በGoogle አገልግሎቶች ላይ ማስታወቂያዎችን ከሚያሳዩ የተወሰኑ ማስታወቂያ ሰሪዎች የሚመጡ ማስታወቂያዎችን ማጥፋት ይችላሉ።

ማስታወቂያዎች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ ለማድረግ ውሂብን መጠቀም

 • የፍለጋ ማስታወቂያዎች ይበልጥ ተገቢነት ያላቸው ለመሆን የእርስዎን እንቅስቃሴ ይጠቀማሉ

  እርስዎ Google ፍለጋን ሲጠቀሙ ማስታወቂያዎች ተገቢ ከሆኑ የፍለጋ ውጤቶች ጋር ሊታዩ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ማስታወቂያዎች እርስዎ ባከናወኑት ፍለጋ እና እርስዎ ባሉበት አካባቢ የሚነቃቁ ናቸው። ለምሳሌ፣ ለ«ቢስክሌቶች» ፍለጋ ካደረጉ በሽያጭ ላይ ያሉ ቢስክሌቶችን የተመለከቱ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ።

  በሌሎች አጋጣሚዎች የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ እንደ ያለፉ ፍለጋዎችዎ ወይም አስቀድመው የጎበኟቸው ጣቢያዎች ያሉ ተጨማሪ ውሂብ ይበልጥ ጠቃሚ እንጠቀማለን። አስቀድመው «ቢስክሌቶች»ን እንደመፈለግዎ መጠን አሁን ደግሞ «ሽርሽር» ብለው ከፈለጉ በሽርሽር ጊዜዎ ላይ ሳሉ በቢስክሌት ለመሄድ የሚችሉባቸው ቦታዎችን የተመለከቱ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ።

 • የGmail ማስታወቂያዎች በእርስዎ እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረቱ ናቸው

  በGmail ውስጥ የሚመለከቷቸው ማስታወቂያዎች ከGoogle መለያዎ ጋር በተጎዳኘ ውሂብ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ለምሳሌ፣ እንደ YouTube ወይም ፍለጋ ባሉ ሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ላይ ያለው እንቅስቃሴዎ በGmail ውስጥ የሚመለከቷቸው የማስታወቂያዎች ዓይነት ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል። Google ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት በገቢ መልዕክት ሳጥንዎ ውስጥ ያሉ ቁልፍ ቃላትን ወይም መልዕክቶችን አይጠቀምም። ማንም ሰው ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ብሎ ኢሜይልዎን አያነብብም።

 • የGoogle Play ማስታወቂያዎች ሊወዷቸው የሚችሏቸው መተግበሪያዎችን እንዲያገኙ ሊያግዘዎት ይችላሉ

  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መተግበሪያዎችን በGoogle Play መደብራችን ላይ ከGoogle እና ከሌሎች ገንቢዎች ማግኘት ይችላሉ። በአንድ የAndroid መሣሪያ ላይ ሲያስሱ ማስታወቂያዎች በእርስዎ የፍለጋ ቃላት፣ በጫኗቸው ወይም በተጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች፣ ወይም እርስዎ እየተመለከቱት መተግበሪያ ጋር ተመሳሳይነት ባለው መተግበሪያ ላይ የተመሠረቱ መስለው ሊታዩ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ «የጉዞ መተግበሪያዎች»ን ከፈለጉ የጉዞ ማቀጃ መተግበሪያ ማስታወቂያ ሊመለከቱ ይችላሉ።

 • የYouTube ማስታወቂያዎች ይበልጥ ተገቢነት ያላቸው ለመሆን የእርስዎን ፍለጋ እና የእይታ እንቅስቃሴ ይጠቀማሉ

  በYouTube ላይ ቪዲዮዎችን ሲመለከቱ በቪዲዮ ገጹ ላይ ማሳትወቂያዎች ቀደም ብለው ሊመለከቷቸው ወይም በመነሻ ገጹ ላይ እንደ ተዛማጅ ቪዲዮዎች ሊያዩዋቸው ይችላሉ። ማስታወቂያዎች እንደ እርስዎ የተመለከቷቸው ቪዲዮዎች፣ የፈለጓቸው ነገሮች ወይም ቦታዎች ወይም እርስዎ በሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች ባለ ውሂብ ላይ የተመሠረቱ ሊሆኑ ይችላሉ።

  ለምሳሌ፣ «የቤት ዲኮር» ብለው ከፈለጉ ወይም ራስዎ-ይስሩ ቪዲዮዎችን ከተመለከቱ የቤት ማሻሻያ ተከታታይ ማስታወቂያ ሊመለከቱ ይችላሉ። እነዚህ ማስታወቂያዎች የሚመለከቷቸው ቪዲዮዎች ፈጣሪዎች ለመደገፍ ያግዛሉ።

  አብዛኛዎቹ የYouTube ማስታወቂያዎችን ማየት ካልፈለጉ ሊዘልሏቸው ይችላሉ ወይም ደግሞ ከማስታወቂያ ነጻ በሆነ YouTube ለመደሰት ለYouTube Premium ደንበኝነት መመዝገብ ይችላሉ።

 • የሸመታ ማስታወቂያዎች እርስዎ የሚፈልጉትን ነገር እንዲያገኙ ያግዙዎታል።

  በGoogle ፍለጋ ላይ አንድ ምርት ሲፈልጉ አንዳንድ ጊዜ የሸመታ ማስታወቂያዎች ከተገቢ የፍለጋ ውጤቶች ጋር አብረን ልናሳይ እንችላለን። ምርቶችን የሚሸጡ ንግዶች እርስዎ የሚፈልጉትን ነገር በፍጥነት እንዲያገኙትና እና መስመር ላይ ወይም በአቅራቢያ ከለ መደብር እንዲገዙት ቀላል ለማድረግ የሸመታ ማስታወቂያዎችን ይጠቀማሉ። እነዚህ ማስታወቂያዎች እርስዎ አሁን በፈለጉት ምርት፣ የእርስዎ አካባቢ፣ ከዚህ በፊት ባሰሷቸው የመስመር ላይ መደብሮች ላይ የተመሠረቱ ናቸው።

  ለምሳሌ፣ «የሌዘር ሶፋ» ብለው ከፈለጉ ከእርስዎ መደብሮች አጠገብ ባሉ የቤት ዕቃዎች መደብሮች ላይ በሽያጭ ላይ ያሉ የሶፋዎች ስዕሎች፣ ዋጋዎች እና የመደብር አካባቢዎች ማስታውቂያዎች ሊመለከቱ ይችላሉ።

 • የአጋር የድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለመፍጠር የእርስዎን የመስመር ላይ እንቅስቃሴ ይጠቀማሉ

  በርካታ ድር ጣቢያዎች እና የሞባይል መተግበሪያዎች ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከእኛ ጋር በአጋርነት ይሠራሉ። እነዚህ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ተጠቃሚዎች ለእኛ ባጋሩትን የግል መረጃ ላይ እና ስለመስመር ላይ እንቅስቃሴዎ በሰበሰብነው ውሂብ ላይ ተመሥርተው የተወሰኑ ማስታወቂያዎችን ለታዳሚዎች «ዓይነቶች» ለማሳየት ይወስናሉ፦ ለምሳሌ፣ «የመጓዝ ፍላጎት ያላቸው ዕድሜያቸው ከ35 እስከ 34 የሚሆኑ ሴቶች»።

  በተጨማሪ እርስዎ በጎበኟቸው ጣቢያዎች ወይም ወደ የእርስዎ የGoogle በመለያ በሚገቡበት ጊዜ ያለን የእርስዎን የChrome አሰሳ እንቅስቃሴ ላይ በመመርኮዝ ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን ልናሳይዎት እንችላለን። ለምሳሌ፣ ወደ የመስመር ላይ የመገበያያ ጋሪዎ ያከሉት፣ በኋላ ላይ ግን ላለመግዛት ስለወሰኑት የእግር ጉዞ ማድረጊያ ጫማ የተመለከቱ ማስታወቂያዎችን ሊመለከቱ ይችላሉ። ሆኖም ግን ይህን የምናደርገው እንደ የእርስዎ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ ወይም የመክፈያ መረጃን ያሉ ማንኛቸውም የግል መረጃዎችን ለማንም ሳናሳይ ነው።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።