ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያቀናብሩ እናግዘዎታለን።

የዛሬ ልጆች እንደ ከዚህ ቀደም የነበሩት ትውልዶች ሳይሆን ከቴክኖሎጂ ጋር በማደግ ላይ ናቸው። በመሆኑን ለቤተሰብዎ ትክክል በሆነ መልኩ ገደቦችን እንዲያበጁ እና ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ በቀጥታ ከባለሙያዎች እና አስተማሪዎች ጋር አብረን እየሠራን ነው።

የወላጅ ክትትል

ዲጂታል የቤት ሕጎችን እንዲያዘጋጁ እርስዎን ማገዝ

Family Link የእርስዎን ታዳጊ ልጆች ወይም ተለቅ ያሉ ልጆች እንዴት መስመር ላይ እንደሚያስሱ እንዲረዱና እንዲሁም መለያዎቻቸውንና ተኳኋኝ መሣሪያዎቻቸውን እንዲያቀናብሩ ሊያግዘዎት ይችላል። ለልጅዎ መተግበሪያዎችን በማቀናበር፣ የማያ ገጽ ጊዜን በመከታተል፣ የመኝታ ሰዓትን በማቀናበር እና ተጨማሪ ነገሮችን በማድረግ ለቤተሰብዎ የሚሰሩ ገደቦችን ማበጀት ይችላሉ።

የበለጠ ለመረዳት

ለቤተሰብ ተስማሚ ተሞክሮዎች

ለቤተሰብ ተስማሚ ተሞክሮዎችን መገንባት

ለቤተሰብዎ ይበልጥ አስደሳች እንዲሆኑ ልዩ ባህሪያትን – እንደ ዘመናዊ ማጣሪያዎች፣ የጣቢያ አጋጆች እና የይዘት ደረጃዎች ያሉ – በአብዛኛዎቹ ምርቶቻችን ውስጥ እንገነባለን።

የበለጠ ለመረዳት

ጠቃሚ ምክሮች ለቤተሰቦች

ልጆች ብልህ እና በራሳቸው የሚተማመኑ የመስመር ላይ ዓለም አሳሽ እንዲሆኑ ማገዝ

Google ልጆች መስመር ላይ የተሻሉ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ ለማስተማር ብልህ፣ የሰለጠኑ ዲጂታል ዜጎች እንዲሆኑ ለማገዝ መርጃዎችን እና ጠቃሚ ምክሮችን ፈጥረናል።

የበለጠ ለመረዳት

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።