ለሁሉም ሰው ቴክኖሎጂን ማቅረብ ማለት ሁሉንም የሚጠቀምበትን ሰው መጠበቅ ማለት ነው።

ሁሉም እኛ የምናደርገው ነገር ሁሉ ተጠቃሚውን ማክበር እንዳለበት Google ያምናል። በይነመረብ እየጎለበተ በሄደ ቁጥር፣ እርስዎን እና የእርስዎን ቤተሰብ መስመር ላይ ደህንነታችሁ እንደተጠበቀ ለማቆየት ማገዝ እንዲቻል የእኛን የደህንነት ቴክኖሎጂዎች እና የግላዊነት መሣሪያዎች በቀጣይነት እናልቃቸዋለን ማለት ነው።

እርስዎን ደህንነት እንደተጠበቀ ለማቆየት እንዲያግዝዎት የምናደርገውን ያስሱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

ሁሉም እኛ የምናደርገው ነገር እንደ አይፈለጌ መልዕክት፣ ማልዌር እና ቫይረሶች የመሳሰሉ ስጋቶች እርስዎ ላይ እንዳይደርሱበት ፈልጎ ለማግኘት እና ለማገድ የሚያግዙ ኃይለኛ አብሮ ገንብ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ጋር ጥበቃ የሚደረግለት ነው። ከአጋሮች እና ከተፎካካሪዎች ጋርም እነዚህን የደህንነት ቴክኖሎጂዎች እናጋራቸዋለን፣ ይህም ሁሉንም ሰው መስመር ላይ ደህነቱ የተጠበቀ እንደሆነ እንዲቆይ የሚያግዙ የኢንዱስትሪውን መስፈርቶች ከፍ ያደርጋሉ።

የበለጠ ለመረዳት

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ውሂብ የGoogle አገልግሎቶች ይበልጥ አጋዥ እና ጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ሆኖም ግን ይህን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም እርስዎን የሚመለከት የግለሰብ ምርጫ ነው። እኛ ምን ውሂብ እንደምንሰበስብ እና እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እና ለምን ጥቅም ላይ እንደሚውል እርስዎ እንዲያውቁት እናደርግዎታለን። ስለዚህ በGoogle መለያ ላይ ኃይለኛ የውሂብ መቆጣጠሪያዎችን ገንብተናል በዚህም ትክክለኛ የሆኑትን የግላዊነት ቅንብሮች እንዲመርጡ ያስችልዎታል።

የበለጠ ለመረዳት

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።

የዛሬ ልጆች እንደ ከዚህ ቀደም የነበሩት ትውልዶች ሳይሆን ከቴክኖሎጂ ጋር በማደግ ላይ ናቸው። በመሆኑም እርስዎ ገደቦችን ማስቀመጥ እና ለእርስዎ ቤተሰብ ትክክል በሆነ መልኩ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንዲችሉ ለማገዝ ከኤክስፐርቶች እና የትምህርት ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በቀጥታ እየሠራን ነው።

የበለጠ ለመረዳት