የእኛ የግላዊነት እና የደህንነት መርሆዎች

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል። ለሁሉም ነጻ እና ተደራሽ የሆኑ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ከመፍጠር ጋር አብሮ የሚመጣ ኃላፊነት ነው። የቴክኖሎጂ ግስጋሴዎች እና የግላዊነት ፍላጎቶች እንደመቀያየራቸው ይህ በተለይ በጣም አስፈላጊ ነው። የእኛን ሰዎች፣ የእኛን የሥራ ሂደቶች፣ እና የእኛን ምርቶች የተጠቃሚን ውሂብ ግላዊነቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንድናደርግ መመሪያ እንዲሰጡን እነዚህን መርሆዎች እንመለከታቸዋለን።

 1. 1. የእኛን ተጠቃሚዎች ያክብሩ። የእነርሱን ግላዊነት ያክብሩ።

  እነዚህ ሐሳቦች ሊነጣጠሉ አይችሉም ብለን እናምናለን። አንድ ላይ በመሆን፣ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ያደረግነውን ነገር እንድናደርግ ተጽዕኖ የፈጠረውን አንድ ነጠላ፣ ዋንኛ እምነትን ይወክላሉ። ሰዎች የእኛን ምርቶች ሲጠቀሙ መረጃዎች በመስጠት በእኛ ላይ እምነት ይጥላሉ በመሆኑም ለእነሱ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው። ምን ዓይነት ውሂብ እንደምንጠቀም፣ እንዴት እንደምንጠቀምበት እና እንዴት ጥበቃ እንደምናደርግለት በሚገባ ተጠንቅቆ ሁልጊዜ ማሰብ ይኖርብናል ማለት ነው።

 2. 2. ምን ውሂብ እንደምንሰበስብ እና ለምን እንደምንሰበስብ ግልጽ ይሁኑ።

  ሰዎች እንዴት የGoogleን ምርቶች እንደሚጠቀሙ በመረጃ ላይ በመመርኮዝ ከውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ለማገዝ ምን ውሂብ እንደምንሰበስብ፣ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እና ለምን እንደሆነ መረዳትን ቀላል ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን። ግልጽ መሆን ማለት ይህን መረጃን በቀላሉ የሚገኝ፣ መረዳት የሚቻል እና ተፈጻሚ ሊሆን የሚችል ማድረግ ማለት ነው።

 3. 3. የእኛን የተጠቃሚዎች የግል መረጃ ለማንም ሰው በጭራሽ አይሽጡ።

  እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች የመሳሰሉ የGoogle ምርቶችን በተቻለ መጠን ጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ውሂብን እንጠቀማለን። በተጨማሪ ተዛማጅነት ያላቸውን ማስታወቂያዎች ለማቅረብ ውሂብን እንጠቀማለን። እነዚህ ማስታወቂያዎች የእኛን አገልግሎቶች የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ ለማቅረብ እና ለሁሉም ሰው በነጻ እንድናቀርባቸው እንድንችል እያገዙ ሳለ የእና ተጠቃሚዎች የግል መረጃ ሊሸጥ እንደማይችል ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

 4. 4. የእነርሱን ግላዊነት እንዲቆጣጠሩ ለሰዎች ቀላል አድርጉላቸው።

  ግላዊነትን በተመለከተ ደግሞ አንድ መጠን ሁሉንም እንደማይመጥን እናውቃለን። እያንዳንዱ የGoogle መለያ በውሂብ ማብሪያ/ማጥፊያ መቆጣጠሪያዎች ጋር ስለሚገነባ የእኛ ተጠቃሚዎች ለእነርሱ ትክክል የሆኑትን የግላዊነት ቅንብሮች መምረጥ ይችላሉ። እና ቴክኖሎጂ በገሠገሠ ቁጥር፣ የእኛ የግላዊነት መቆጣጠሪያዎች አብረው ይገሠግሣሉ፣ ግላዊነቱ ሁልጊዜ የተጠቃሚው የግል ምርጫ መሆኑን ይቀጥላል።

 5. 5. ሰዎች የእነርሱን ውሂብ እንዲገመግሙ፣ እንዲያንቀሳቅሱ ወይም እንዲሰርዙ ሰዎችን ሥልጣን ይስጧቸው።

  ሁሉም ተጠቃሚ ከእኛ ጋር ወደ አጋሩት የግል መረጃ መዳረሻ – በማናቸውም ጊዜ እና በማናቸውም ምክንያት ሊኖራቸው ይገባል ብለን እናስባለን። ለዚህም ነው ሰዎች ወደ የእነርሱ ውሂብ እንዲደርሱበት እና እንዲገመግሙት፣ እንዲያውርዱ እና ከፈለጉ ወደ ሌላ አገልግሎት እንዲያዛውሩት ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲሰርዙት ቀላል እንዲሆንላቸው መሥራታችንን የምንቀጥለው።

 6. 6. ወደ የእኛ ምርቶች ጠንካራ የሆኑ የደህንነት ቴክኖሎጂዎችን ይገንቡ።

  የእኛን ተጠቃሚዎች ግላዊነት መጠበቅ ማለት ለእኛ በአደራ የሰጡንን ውሂብ መጠበቅ ማለት ነው። እያንዳንዱን የGoogle ምርት እና አገልግሎት ደህንነቱ እንደተጠበቀ ለማቆየት፣ በዓለም ውስጥ ከማንም በላይ የላቁትን የደህንነት መጠበቂያ መሠረተ ልማቶች በምሕንድስና መፍጠር እና ተግባራዊ ማድረጋችንን እንቀጥላለን። ይህ ማለት በመጠንሰስ ላይ ያሉ የመስመር ላይ ስጋቶች ጎልብተው የእኛ ተጠቃሚዎች ላይ ከመድረሳቸው በፊት ፈልጎ ለማግኘት እና ለእነርሱ ጥበቃ ለማድረግ ሲባል በቀጣይነት የእኛን አብሮ-ገንብ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎችን ማላቅ እና ማጠናከር ማለት ነው።

 7. 7. ለሁሉም ሰው የመስመር ላይ ደህንነትን ለማላቅ በምሳሌነት መሪ ይሁኑ።

  መስመር ላይ ተጠቃሚዎችን ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ማቆየት Googleን አያስቆምም – ወደ መላው በይነመረብ ይራዘማል። Google ዛሬ የምንጠቀምባቸውን በርካታዎቹን የደህንነት መጠበቂያ መስፈርቶች በመፍጠር የመጀመሪያው ኩባንያ ነበር እና በሁሉም ሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎችን እንደ አዲስ መፍጠራችንን እንቀጥላለን። በበይነ መረብ ዙሪያ መለስ ደህንነት በኢንዱስትሪው ዙሪያ መለስ ትብብርን ስለሚጠይቅ የእኛን የደህንነት መጠበቂያ ትምህርቶች፣ ተሞክሮዎች፣ እና መሣሪያዎች ከእኛ አጋሮች፣ ድርጅቶች እና ተፎካካሪዎች ጋር በመላው ዓለም ዙሪያ እናጋራቸዋለን።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።