እርስዎ ነዎት ተቆጣጣሪ

ግላዊነትን በተመለከተ አንድ መፍትሔ ለሁሉም ሊሆን እንደማይችል እናውቃለን፣ ስለዚህ ኃይለኛና ለመጠቀም ቀላል የሆኑ የግላዊነት መሣሪያዎችን ወደ የእርስዎ Google መለያ ገንብተናል። ለእርስዎ ትክክል በሆኑ የግላዊነት ቅንብሮች እና በመላ አገልግሎቶቻችን ላይ ምን የውሂብ አይነቶችን እንደምንሰበስብና እንደምንጠቀም ላይ ቁጥጥር ላይ ይሰጡዎታል።

ውሂብ በመላ Google ላይ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ይቆጣጠሩ

 • በGoogle መለያዎ ውስጥ የተቀመጠው ውሂብ ይቆጣጠሩ

  የእርስዎን መረጃ፣ ግላዊነት እና የደህንነት ቅንብሮች ሁሉ በአንዲት ቦታ ላይ ሊያገኟቸው ይችላሉ – የእርስዎ Google መለያ። እንደ ዳሽቦርድ እና የእኔ እንቅስቃሴ ያሉ ለመጠቀም ቀላል የሆኑ መሣሪያዎችን ፈጥረናል፣ እነዚህም በመላ Google አገልግሎቶችዎ ላይ ካለው እንቅስቃሴዎች በተሰበሰበው ውሂብ ላይ ግልጽነት ይሰጡዎታል። እንዲሁም እንደ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች እና የማስታወቂያ ቅንብሮች ያሉ ኃይለኛ የግላዊነት መቆጣጠሪያዎች አሉ፣ እነዚህ እርስዎ Google ለእርስዎ እንዴት በተሻለ ሁኔታ እንደሚሰራልዎ ለመወሰን የውሂብ መሰብሰብና ጥቅም ላይ መዋልን እንዲያበሩ ወይም እንዲያጠፉ ያስችሉዎታል።

 • በግላዊነት ፍተሻዎ አማካኝነትን ለእርስዎ ትክክለኛ የሆኑ የግላዊነት ቅንብሮችን ይምረጡ

  በጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የምንሰበስበው የውሂብ አይነቶች ማቀናበር፣ ለጓደኛዎች ምን እንደሚያጋሩ ወይም ምን ይፋ እንደሚያደርጉ ማዘመን፣ እና እንድናሳየዎት የሚፈልጓቸው የማስታወቂያዎች አይነቶችን ማስተካከል ይችላሉ። እነዚህን ቅንብሮች የፈለጉትን ያህል ጊዜ በመደጋገም መቀየር እና እንዲሁም የአሁኑ ቅንብሮችዎን ከግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ለማገዝ መደበኛ አስታዋሾችን መምረጥ ይችላሉ።

 • ምን ውሂብ በመለያዎ ላይ እንደሚቀመጥ እንዲመርጡ የሚያስችሉዎ ቀላል የማብሪያ/ማጥፊያ መቆጣጠሪያዎች

  በካርታዎች ውስጥ ካሉ ከተሻሉ የመጓጓዣ አማራጮች ጀምሮ እስከ በፍለጋ ውስጥ ይበልጥ ፈጣን ውጤቶች ድረስ በመለያዎ ላይ የምናስቀምጠው ውሂብ የGoogle አገልግሎቶች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይችላል። የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎችን በመጠቀም በመላ የGoogle አገልግሎቶች ላይ ያለዎት ተሞክሮን ግላዊነት ለማላበስ ከመለያዎ ጋር ምን እንደሚጎዳኝ መምረጥ እና የተወሰኑ ውሂብ ዓይነቶችን – እንደ የእርስዎ ፍለጋ እና የአሰሳ እንቅስቃሴ፣ የአካባቢ ታሪክ እና ከእርስዎ ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ጡባዊ የሚገኝ መረጃን ያሉ – ማሰባሰብ ባለበት ማቆም ይችላሉ።

 • በየእኔ እንቅስቃሴ ላይ በእርስዎ መለያ ውስጥ ምን ውሂብ እንዳለ ይመልከቱ እና ይቆጣጠሩ

  የእኔ እንቅስቃሴ እርስዎ የፈለጓቸውን፣ የተመለከቷቸውን እና አገልግሎቶቻችን በመጠቀም የተመለከቷቸውን ሁሉም ነገሮች ማግኘት የሚችሉበት ማእከላዊ ቦታ ነው። ያለፈ የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎን ማስታወስ ቀላል ለማድረግ በርዕሶች፣ ቀን እና ምርት የሚፈልጉባቸውን መሣሪያዎች እንሰጠዎታለን። የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ወይም ሌላው ሳይቀር ከእርስዎ መለያ ጋር እንዲጎዳኙ የማይፈልጓቸውን ሙሉ ርዕሶች በቋሚነት መሰረዝ ይችላሉ።

 • በዳሽቦርድ ውስጥ በGoogle መለያዎ ውስጥ ያለውን ውሂብ ይመልከቱ እና ያቀናብሩ

  እርስዎ የሚጠቀሙባቸው የGoogle ምርቶች እና በእያንዳንዳቸው ውስጥ ያለ የውሂብ አጠቃላይ እይታ መመልከት ቀላል እናደርገዋለን፣ ሁሉም በአንዲት ቦታ ላይ። ባለፈው ወር ውስጥ የነበረው የGoogle እንቅስቃሴዎ መገምገም ይችላሉ፤ ስንት ኢሜይሎች፣ ሰነዶች እና ፎቶዎች እንዳለዎት ይመልከቱ፤ እና ስለGmail ቅንብሮች ላሉ ጥያቄዎች መልሶችን ያግኙ። እርስዎ እንዲሁም ፈጣን መዳረሻ የሚመለከታቸው የምርት ቅንብሮች እና ካስፈለገዎት የተዛማጅ እገዛ ማዕከል ጽሑፎች አለዎት።

 • «ውሂብዎን ያውርዱ»ን በመጠቀም የእርስዎን ይዘት ወደ የፈለጉበት ቦታ ይዘውት ይሂዱ

  የእርስዎ ፎቶዎች። የእርስዎ ኢሜይሎች። የእርስዎ እውቂያዎች። እንዲያውም የእርስዎ ዕልባቶች ጭምር። በGoogle መለያዎ ላይ የውሂብ ተቆጣጣሪ እርስዎ ነዎት። ለዚህ ነው ውሂብዎን ያውርዱን የፈጠርነው – በዚህም ቅጂ መስራት፣ ምትኬ ማስቀመጥ ወይም እንዲያውም ወደ ሌላ አገልግሎት መውሰድ ይችላሉ።

  ውሂብን Google ፎቶዎች፣ Drive፣ ቀን መቁጠሪያ፣ Google Play ሙዚቃ እና Gmail ጨምሮ በበርካታ ቅርጸቶች ማውረድ ይችላሉ። ወይም ደግሞ ውሂቡን Dropbox፣ Microsoft OneDrive እና Box ጨምሮ በቀጥታ ወደ አገልግሎቶች መላክ ይችላሉ።

 • ሌሎች እርስዎን እንዲያገኙ ለማቅለል ምን መሠረታዊ መረጃ እንደሚያጋሩ ይወስኑ

  ሌሎች እርስዎን እንደ Hangouts፣ Gmail እና ፎቶዎች ባሉ የGoogle አገልግሎቶች ላይ እንዲያገኙ ለማገዝ እርስዎ እንደ የእርስዎ ስም፣ ኢሜይል እና ስልክ ቁጥር ያለ የግል መረጃዎን ማቀናበር ይችላሉ።

 • Google ለእርስዎ ግላውነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ምን መረጃ እንደሚጠቀም ይቆጣጠሩ

  በማስታወቂያ ቅንብሮች ውስጥ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ግላዊነት ለማላበስ የምንጠቀምበት ውሂብ መቆጣጠር ቀላል እናደርግልዎታለን። ይህ ወደ የGoogle መለያዎ ያከሉት መረጃ፣ በእንቅስቃሴዎ አማካኝነት ስለፍላጎቶችዎ ያደረግናቸው ግምቶች እና ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከእኛ ጋር አጋር ከሆኑ ሌሎች ማስታወቂያ ሰሪዎች ጋር ያሉ መስተጋብሮችን ያካትታል።

  የእርስዎ እንቅስቃሴ ምን እንደምናሳየዎት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል፣ ነገር ግን እርስዎ ነዎት ሁልጊዜ ተቆጣጣሪ የሆኑት። ለምሳሌ፣ በYouTube ላይ የቅርብ ጊዜ ግጥሚያ ድምቀቶችን ስለተመለከቱ ወይም በGoogle ፍለጋ ላይ «ከእኔ አጠገብ ያሉ የእግር ኳስ ሜዳዎች» ስለፈለጉ የእግር ኳስ አድናቂ እንደሆኑ ልናስብ እንችላለን። እና በአንድ የአጋር ማስታወቂያ ሰሪ ድር ጣቢያ ላይ የተወሰነ ጊዜ ከወሰዱ በዚያ ጉብኝት ላይ ተመስርተን ማስታወቂያቆችን ልንጠቁም እንችላለን።

  ማስታወቂያን ግላዊነት ማላበስ ሲበራ ማንኛውም መረጃ መምረጥ – ዕድሜ እና ጾታ፣ የተገመተ ፍላጎት ወይም ከዚህ ቀደም ከአንድ ማስታወቂያ ሰሪ ጋር የነበረ መስተጋብር – ለምን ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ ተጨማሪ ማወቅ ወይም ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን በአጠቃላይ ማቦዘን ይችላሉ። አሁንም ማስታወቂያዎችን ይመለከታሉ፣ ነገር ግን ተገቢነታቸው ያነሰ የመሆኑ ዕድል ከፍ ይላል።

 • ማንነትን በማያሳውቅ ሁነታ በይነመረቡን በግል ያስሱ

  የእርስዎ የመስመር ላይ ታሪክ የእርስዎን የፍለጋ ውጤቶች ይበልጥ ጠቃሚ ለማድረግ ሊያግዝ ይችላል፣ ነገር ግን በግል ማሰስ የሚፈልጉባቸው ጊዜዎች ይኖራሉ። ለምሳሌ፣ ከአጋር ጋር ኮምፒውተር የሚጋሩ ከሆኑ እየፈለጉ ያሉትን ያልታሰበ የልደት ቀን ስጦታ የእርስዎ የአሰሳ ታሪክ እንዲያበላሽብዎት ላይፈልጉ ይችላሉ። እንደዚህ ላሉ ጊዜያት Chrome የእርስዎን የአሰሳ ታሪክ እንዳያስቀምጥ ለመከላከል በእርስዎ ኮምፒውተር ወይም ተንቀሳቃሽ መሣሪያ ላይ ማንነትን የማያሳውቅ መስኮት ይክፈቱ።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።