ዲጂታል የቤት ሕጎችን እንዲያዘጋጁ እርስዎን ማገዝ

Family Link የእርስዎን ታዳጊ ልጆች ወይም ተለቅ ያሉ ልጆች እንዴት መስመር ላይ እንደሚያስሱ እንዲረዱና እንዲሁም መለያዎቻቸውንና ተኳኋኝ መሣሪያዎቻቸውን እንዲያቀናብሩ ሊያግዘዎት ይችላል። ለልጅዎ መተግበሪያዎችን በማቀናበር፣ የማያ ገጽ ጊዜን በመከታተል፣ የመኝታ ሰዓትን በማቀናበር እና ተጨማሪ ነገሮችን በማድረግ ለቤተሰብዎ የሚሰሩ ገደቦችን ማበጀት ይችላሉ።

በFamily Link አማካኝነት መስመር ላይ ለቤተሰብዎ ገደቦችን ያብጁ

 • የማያ ገጽ ሰዓቱን ይከታተሉ

  ለልጅዎ ትክክለኛው የማያ ገጽ ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ እርስዎ ይወስኑ። መሣሪያቸውን እንደ መጽሐፍ ለማንበብ፣ ቪዲዮዎችን ለመመልከት ወይም ጨዋታዎችን ለመጫወት እንደሆነ የሚጠቀሙበት ባሉ ነገሮች ላይ ሊወሰን ይችላል። ልጅዎ አብዛኛው ጊዜ የትኛዎቹን መተግበሪያዎች እየተጠቀሙ እንደሆነ ለማየት የFamily Link መተግበሪያ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን ይጠቀሙ።

 • ዕለታዊ መዳረሻን ይገድቡ

  ዕለታዊ ገደብ ያቀናብሩ – Family Link በልጅዎ የAndroid መሣሪያ ላይ ዕለታዊ የጊዜ ገደቦችን እንዲያቀናብሩና የሚተኙበት ሰዓት ሲደርስ መሣሪያቸውን የሚቅልፉበት የመኝታ ሰዓት እንዲያቀናብሩ ያስችልዎታል።

 • የልጅዎን መሣሪያ በርቀት ይቆልፉ

  የጨዋታ፣ የጥናት ወይም የእንቅልፍ ሰዓት ሲሆን መሣሪያዎቻቸውን ያቀናብሩ ወይም የተወሰኑ መተግበሪያዎችን ይደብቁ።

ልጆችዎ መስመር ላይ ምን ማግኘት እንደሚችሉ መዳረሻን ያቀናብሩ

 • የልጅዎን የመለያ ቅንብሮች በGoogle ረዳቱ ላይ መጠቀም

  ልጆች በራሳቸው መለያ በረዳት ወደነቁ መሣሪያዎች መግባት ይችላሉ፣ ይህ በFamily Link የሚተዳደር ነው። የራሳቸው ግላዊነት የተላበሰ የረዳት ተሞክሮ ያገኛሉ፣ እና ለቤተሰቦች የተነደፉ ጨዋታዎችን፣ እንቅስቃሴዎችን እና ታሪኮችን መድረስ ይችላሉ። ልጆች ግብይቶችን እንዳያከናውኑ ይታገዳሉ፣ እና ወላጆች ልጆቻቸው በረዳቱ ላይ የሶስተኛ ወገን ተሞክሮዎች መዳረሻ ይኖራቸው እንደሆነ መወሰን ይችላሉ።

 • ልጅዎ ያላቸው የድር ጣቢያዎች መዳረሻን በChrome ያቀናብሩ

  ልጅዎ በAndroid ወይም ChromeOS መሣሪያዎቻቸው ላይ የChrome አሳሻቸውን ሲጠቀሙ ልጅዎ ያላቸው የድር ጣቢያዎች መዳረሻን ማቀናበር ይችላሉ። ልጅዎን እርስዎ ቅር በማይሉዎ ድር ጣቢያዎች መገደብ ወይም እንዲጎበኟቸው የማይፈልጓቸው የተወሰኑ ጣቢያዎችን ማገድ ይችላሉ።

 • በSafeSearch ማጣሪያዎች አማካኝነት በGoogle ፍለጋ ላይ ግልጽ ጣቢያዎችን ያግዱ

  የFamily Link አካል እንደመሆንዎ መጠን በመላ ስልኮች፣ ጡባዊዎች እና ላፕቶፖች ላይ የSafeSearch ቅንብሩን መጠቀም ይችላሉ። ይህ ቅንብር የወሲብ ስራ እና ግልጽ ጥቃትን ለመከላከል ግልጽ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎች እና ድር ጣቢያዎችን ከGoogle ፍለጋ ውጤቶች ለማገድ የተነደፈ ነው፣ ምንም እንኳ 100% ትክክል ባይሆንም። የSafeSearch ቅንብሩ በነባሪነት በመለያ ለገቡ ከ13 ዓመት (ወይም በአገርዎ ከሚመለከተው ዕድሜ) በታች ለሆኑ፣ በFamily Link የሚቀናበሩ መለያዎች ላላቸው ተጠቃሚዎች ይበራል፣ ነገር ግን ወላጆች ለማጥፋት መምረጥ ይችላሉ።

ቤተሰቦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተገነቡ መተግበሪያዎችን ያግኙ

 • ልጅዎ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን መተግበሪያዎች ለማስተዳደር Family Linkን ይጠቀሙ

  ሁሉም መተግበሪያዎች ለሁሉም ልጆች ጥሩ ናቸው ማለት አይደለም። ከFamily Link ጋር እርስዎ ተገቢነት አለው ብለው በሚያስቡት የደረጃ አሰጣጥ ጋር ብቻ መተግበሪያዎችን የእርስዎ ልጅ እንዲያስስ ለመፍቀድ በGoogle Play መደብር ውስጥ መተግበሪያዎችን ማጣራት ይችላሉ። ልጅዎ ከGoogle Play መደብር ለማውረድ የሚፈልጉትን መተግበሪያዎች እንዲያጸድቁ ወይም እንዲያግዱ የሚያስችልዎ ማሳወቂያ በመሣሪያዎ ላይ ያግኙ።

  ለእርስዎ ልጅ የትኛዎቹ የይዘት ክፍሎች ወይም መዝናኛዎች ተገቢነት እንዳላቸው እርስዎ እንዲወስኑ ለማገዝ በGoogle Play ላይ ያሉትን የቤተሰብ ኮከብ ባጆች ይፈልጉ። የቤተሰብ ኮከብ ይበልጥ ጥንቃቄ በተሞሉ ግምገማዎች ሥር እንዳለፉ እና ቤተሰቦችን ከግምት በማስገባት እንደተገነቡ መልዕክት ያስተላልፋሉ። በተጨማሪ የእሱን ይዘት ደረጃ አሰጣጦች፣ ፈቃዶች እና ማስታወቂያዎችን ወይም ውስጠ መተግበሪያ ግዢዎችን በውስጡ መያዝ አለመያዙን መገምገም ይችላሉ።

  በተጨማሪ ወላጆች የማያ ገጽ ጊዜን ብዛት ብቻ ሳይሆን የማያ ገጽ ጊዜን ጥራት ማስተዳደር እንዲችሉ ማገዝ እንፈልጋለን። ይህም ስለሆነ ነው በFamily Link ውስጥ የእርስዎ ልጆች እርስዎ ጥሩ ስሜት በሚሰማዎት ይዘት እንዲሰማዎት የሚያስችል ጥራት ያለው ይዘትን በማግኘት መዝናናት እንዲችሉ ከትክክለኛ መምህራን ከተገኙ ጠቃሚ ምክሮች ጋር ገንቢ የሆነ ይዘትን ፈልገው እንዲያገኙ እርስዎን ሊያግዙ የሚችሉ ባሕሪያትን የገነባነው።

ለልጅዎ ምን ትክክል እንደሆነ ለመምረጥ የመለያ ቅንብሮችን ይጠቀሙ

 • የልጅዎን መለያ ማቀናበር እና ደህንነት መጠበቅ

  በFamily Link አማካኝነት የልጅዎ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች – እርስዎ እንዳሉዎት ያሉ – ምን እንቅስቃሴ እንደሚቀመጥና አገልግሎቶቻችን ሲጠቀሙ ማን የልጅዎን Google መለያ እንደሚያቀናብር እንዲወስኑ ያስችልዎታል።

  ወላጅ እንደመሆንዎ መጠን ልጅዎ የይለፍ ቃላቸውን ከረሱት ዳግም እንዲያስጀምሩት ሊያግዟቸው ይችላሉ። እንዲሁም አስፈላጊ ከመሰለዎት የልጅዎን የግል መረጃ ማርትዕ ወይም እንዲያውም መለያቸውን መሰረዝ ይችላሉ። ያለፈቃድ ሌላ መገለጫ ወደ መለያቸው ወይም መሣሪያቸው ማከል አይልቹም። በመጨረሻም፣ የAndroid መሣሪያቸው አካባቢ ማየት ይችላሉ (እስከበራ፣ ከበይነመረብ ጋር እስከተገናኘ እና በቅርቡ ገቢር እስከነበረ ድረስ)።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።