ምን ውሂብ እንደምንሰበስብ እና ለምን እንደምንሰበስብ መረዳት ቀላል ማድረግ

የGoogle አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎን ውሂብ በተመለከተ በእኛ ላይ እምነት ይጥላሉ። አገልግሎቶቻችን ለእርስዎ የተሻለ ለማድረግ ብለን ስለምንሰበስበው ውሂብ፣ እንዴት እና ለምን እንደምንጠቀምበት ግልጽ መሆን የእኛ ኃላፊነት ነው።

ስለምንጠቀምበት ውሂብ ግልጽ መሆን

 • አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ እኛ የምንሰበስበው መረጃ

  አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ – ለምሳሌ፣ በGoogle ላይ ፍለጋ ሲያከናውኑ፣ በGoogle ካርታዎች ላይ አቅጣጫዎችን ሲያገኙ፣ ወይም በYouTube ላይ ቪዲዮ ሲመለከቱ – እነዚህ አገልግሎቶች እንዲሠሩልዎ ለማድረግ ውሂብ እንሰበስባለን። ይህ እነዚህ ሊያካትት ይችላል፦

  • ፍለጋ ያደረጉባቸው ነገሮች
  • የተመለከቷቸው ቪዲዮዎች
  • የሚመለከቷቸው ወይም ጠቅ የሚያደርጓቸው ማስታወቂያዎች
  • የእርስዎ አካባቢ
  • የሚጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች
  • የGoogle አገልግሎቶችን ለመድረስ የሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች፣ አሳሾች እና መሣሪያዎች
 • እርስዎ የሚፈጥሯቸው ወይም ለእኛ የሚያጋሩት መረጃ

  ለአንድ የGoogle መለያ ሲመዘገቡ የግል መረጃ ያቀርቡልናል። በመለያ ገብተው ከሆነ አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ የሚፈጥሩትን መረጃ እንሰበስብና እንጠብቃለን። ይህ እነዚህን ሊያካትት ይችላል፦

  • የእርስዎ ስም፣ የልደት ቀን እና ጾታ
  • የእርስዎ የይለፍ ቃል እና ስልክ ቁጥር
  • በGmail ላይ የሚጽፏቸው እና የሚቀበሏቸው ኢሜይሎች
  • እርስዎ የሚያስቀምጧቸው ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች
  • በDrive ላይ የሚፈጥሯቸው ሰነዶች፣ ሉሆች እና ስላይዶች
  • በYouTube ላይ የሚጽፏቸው አስተያየቶች
  • እርስዎ ያከሏቸው እውቂያዎች
  • የቀን መቁጠሪያ ክስተቶች

የGoogle አገልግሎቶች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ ለማድረግ ውሂብን መጠቀም

 • Google ካርታዎች እንዴት የእርስዎን ቦታዎች በበለጠ ፍጥነት እንደሚያገኝልዎ

  የGoogle ካርታዎች መተግበሪያውን በሚጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ስልክ ስለአካባቢዎ ያለ ስም-አልባ የውሂብ ቅንጥብጣቢዎች ለGoogle መልሶ ይልካል። ይሄ የትራፊክ ሥርዓተ ጥለቶችን ለይቶ ለማወቅ በእርስዎ ዙሪያ ከሚገኙ ሰዎች ከተገኘ ውሂብ ጋር ይጣመራል። ለምሳሌ፣ በርካታ ተሽከርካሪዎች በተመሳሳዩ ጎዳና ላይ ዝግ ብለው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ካርታዎች ለይቶ ሊያውቅ እና ከባድ ትራፊክ እንዳለ ሊያሳውቀዎት ይችላል። ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ካርታዎች አደጋ እንዳለ ሲያስጠነቅቀዎት እና ይበልጥ ፈጣን ወደ ሆነ የጉዞ መስመር ሲመራዎት ከሌሎች የእርስዎ ቢጤ አሽከርካሪዎች የተገኘው ውሂብን ነው የሚያመሰግኑት።

 • Google እንዴት የእርስዎን ፍለጋዎች በራስ-እንደሚያጠናቅቅ

  የሆነ ነገር ሲፈልጉ እና ፊደል ሲሳሳቱ ያውቃሉ – እና እንዲህም ሆኖ Google ምን ለማለት እንደፈለጉ ያውቃል? የፊደል ማረሚያ ሞዴላችን ለእርስዎ ለማረም ከዚህ በፊት ተመሳሳዩን ስህተት ከተሳሳቱ ሰዎች የመጣ ውሂብን ይጠቀማል። እርስዎ «Barsalona» ብለው ሲተይቡ «Barcelona» ለማለት እንደፈለጉ የምናውቀው በዚህ መንገድ ነው።

  የእርስዎ የፍለጋ ታሪክ እንዲሁም Google ፍለጋዎችዎን በራስ-እንዲያጠናቅቁ ሊያግዝ ይችላል። ለምሳሌ፣ ከዚህ በፊት «Barcelona flights»ን ፈልገው ከሆነ ተይበው ሳይጨርሱ ሁሉ ይህን በፍለጋ ሳጥኑ ውስጥ ልንጠቁም እንችላለን። ወይም ደግሞ የእግር ኳስ ክለብ አድናቂ ከሆኑና አብዛኛው ጊዜ «Barcelona scores»ን የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን ወዲያውኑ ልንጠቁም እንችላለን።

 • YouTube እርስዎ ለማየት የሚፈልጓቸውን ቪዲዮዎችን እንዴት እንደሚያገኝ

  YouTube ከዚህ በፊት በተመለከቷቸው እና ተመሳሳይ የማየት ልማዶች ያላቸው ሌሎች ሰዎች ከዚህ በፊት በተመለከቱት ላይ ተመስርቶ እርስዎ ሊወዷቸው የሚችሏቸውን ቪዲዮዎች ይመክራል። እንዲሁም ሁሉም ሰው በሚመለከተው ላይ ተመስርተን ምን ታዋቂ እንደሆነ እና ምን በመታየት ላይ እንዳለ ፍንጮችን እናገኛለን። ይህ በተለያዩ ዘውጎች ላይ እርስዎ የሚያማርጡባቸው ቪዲዮዎችን – እንደ ከፍተኛ የሙዚቃ ትራኮች፣ የእንዴት እንደሚደረጉ መማሪያዎች እና ዜና ያሉ – እንድንጠቁም ያግዘናል።

 • Chrome እንዴት ቅፆችን እንደሚሞላልዎ

  ግዢ በፈጸሙ ወይም መስመር ላይ ለአንድ መለያ በተመዘገቡ ቁጥር እያንዳንዱ ጊዜ የግል መረጃዎን በመስጠት ቅፆችን በመሙላት ጊዜ ያጠፋሉ። Chromeን ሲጠቀሙ እኛ እነዚህን ቅፆች በራስ-መሙላት እንድንችል የእርስዎን ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ የኢሜይል አድራሻ፣ እና የክፍያ መረጃ የመሳሰሉ ነገሮችን ማስቀመጥ እንችላለን። በማንኛውም ጊዜ የተወሰኑ በራስ-ሰር የሚሞሉ መስኮችን ማርትዕ ወይም ይህን ቅንብር ሙሉ በሙሉ ማሰናከል ይችላሉ።

 • Google ፍለጋ እንዴት የራስዎን መረጃ እንዲያገኙ እንደሚያግዘዎት

  Google ፍለጋ ከGmail፣ ከGoogle ፎቶዎች፣ ቀን መቁጠሪያ እና ተጨማሪ ነገሮች ጠቃሚ መረጃን ሊያወጣ እና መረጃውን እርስዎ ቆፍረው ማውጣት እንዳይኖርብዎ ለማገዝ በእርስዎ የግል የፍለጋ ውጤቶች ውስጥ ለእርስዎ ያሳይዎታል። በቀላሉ እንደ «የእኔ የጥርስ ሐኪም ቀጠሮ»፣ «በባሕር ዳርቻ የተነሳኋቸውን ፎቶዎች አሳየኝ» ወይም «ክፍል ያስያዝኩበት ሆቴል የት አለ» ላሉ ነገሮች ፍለጋ ያድርጉ። በመለያ እስከገቡ ድረስ ይህን መረጃ ከሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ጎትተን እናወጣው እና በአንድ እርምጃ እርስዎ እንዲያገኙት እናደርጋለን።

 • ነገሮችን እንዲያከናውኑ የእርስዎ የGoogle ረዳት እንዴት ሊያግዝዎት እንደሚችል

  በቤትዎ ውስጥ ቢሆኑም ወይም መንገድ ላይ የእርስዎ ረዳት ለማገዝ ሁልጊዜ ዝግጁ ነው። የእርስዎን ረዳት ጥያቄ ሲጠይቁ ወይም ማን ማድረግ እንዳለበት ሲነግሩት፣ እርስዎ የሚፈልጉትን ለማግኘት ከሌሎች የGoogle አገልግሎቶች የሚገኝ ውሂብን ይጠቀማል ለምሳሌ፣ «በአቅራቢያ ምን ካፌዎች አሉ?» ብለው ቢጠይቁ ወይም «ነገ ዣንጥላ ያስፈልገኛል?» ቢሉ የእርስዎ ረዳት በጣም ተዛማጅነት ያለውን መልስ ለመስጠት ከካርታዎች እና ፍለጋ እንዲሁም ከእርስዎ የአካባቢ ፍላጎቶች እና ምርጫዎች የሚገኝ መረጃን ይጠቀማል። ከእርስዎ ረዳት ጋር በሚደረግ መስተጋብር የሚሰበሰብን ውሂብ ለማየት ወይም ለመሰረዝ ሁልጊዜ በእርስዎ Google ረዳት ውስጥ ያለውን የእኔ እንቅስቃሴ መሣሪያ መጎብኘት ይችላሉ።

የእርስዎን ግላዊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ምርቶችን መገንባት

 • የግላዊነት ግምገማ በእኛ የምርት ግንባታ ላይ ቁልፍ እርምጃ ነው

  ለማናቸውም አዲስ የምርት ማስጀመር በእኛ የውስጥ ግላዊነት ቡድን እና ሁሉን አቀፍ የግምገማ ሂደት ላይ እንተማመናለን። ግላዊነትን ቁልፍ ቦታ የሚሰጠው በማድረግ ሂደት ላይ – ከምሕንድስና ጀምሮ እስከ ምርት አስተዳደር ድረስ በእያንዳንዱ የምርት ግንባታ ላይ ቁርጠኛ የሆነ ትኩረት እንሰጣለን። ይህ በየቀኑ ሰዎች የሚዝናኑባቸውን የGoogle ምርቶች ማመን እንደሚችሉ ለማረጋገጥ ይረዳል።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።