ለቤተሰብ ተስማሚ ተሞክሮዎችን መገንባት

ለቤተሰብዎ ይበልጥ አስደሳች እንዲሆኑ ልዩ ባህሪያትን – እንደ ዘመናዊ ማጣሪያዎች፣ የጣቢያ አጋጆች እና የይዘት ደረጃዎች ያሉ – በአብዛኛዎቹ ምርቶቻችን ውስጥ እንገነባለን።

ለልጆች ይዘትን እና ተሞክሮዎችን ማግኘት

 • በYouTube ለልጆች አማካኝነት የመማር እና የመዝናናት ዓለም ይወቁ

  YouTube ለልጆችን የፈጠርነው በመላው ዓለም ላይ ያሉ ልጆች ፍላጎቶቻቸውን በመስመር ላይ ቪዲዮዎች ማሰስ የሚችሉበት ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ እንዲሆን ነው። እርስዎ በወላጅ መቆጣጠሪያዎች መሣሪያ ስብስቦች በኩል አዝናኝ የሆነ የቤተሰብ ተሞክሮዎችን እንዲያሰባስቡ ቀላል እናደርግልዎታለን፦

  • ልጅዎ ለምን ያህል ጊዜ ቪዲዮዎችን መመልከት እንደሚችሉ ላይ ገደቦችን ለማስቀመጥ ሰዓት ቆጣሪ ያቀናብሩ።
  • ልጆችዎ በታመኑ ሶስተኛ ወገኖች ወይም በYouTube ለልጆች ቡድኑ የተመረጡ የሰርጦች ስብስቦችን ብቻ እንዲመለከቱ ይፍቀዱ።
  • ልጆችዎ በ«እንደገና ይመልከቱት» ውስጥ በቅርቡ የተመለከቷቸውን ነገሮች ይከታተሉ።
  • በYouTube ለልጆች ቡድን የተረጋገጡ ይበልጥ የተወሰነ የሰርጦች ተሞክሮን ለማግኘት ፍለጋን ያጥፉ።
  • ቪዲዮዎች ወይም ሰርጦች በልጆችዎ መተግበሪያ ላይ እንዳይታዩ ያግዷቸው።
  • በመተግበሪያው ውስጥ መሆን የለባቸምው የሚሏቸው ቪዲዮዎች ካሉ ለግምገማ ይጠቁሟቸው።

  በYouTube ለልጆች ላይ ያሉ ቪዲዮዎች ለቤተሰብ ተስማሚ እንደሆኑ ለማቆየት በአንድ ላይ የማጣሪያዎች፣ የተጠቃሚ ግብረመልስ እና የሰው ገምጋሚዎች ቅልቅል እንጠቀማለን። ነገር ግን ፍጹም የሆነ ስርዓት የለም፣ እና አግባብ ያልሆኑ ቪዲዮዎች ሾልከው ሊያልፉ ይችላሉ፣ ስለዚህ ጥበቃዎቻችን ለማሻሻል እና ይበልጥ ተጨማሪ የወላጅ መቆጣጠሪያዎችን ለማቅረብ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ እይሰራን ነው።

 • በGoogle Play ላይ ለቤተሰቦች ተስማሚ የሆነ ቦታን መፍጠር

  ለልጅዎ ምን ትክክል እንደሆነ እንዲወስኑ ለማገዝ ግምገማዎችን ያንብቡና በመተግበሪያዎች እና ጨዋታዎች ላይ የቤተሰብ ኮከብ ባጁን ይፈልጉ። የኮከብ ባጁ ይዘቱ በበለጠ ጥንቃቄ የተገመገመና ልጆችን ታሳቢ በማድረግ የተገነባ እንደሆነ ያመለክታል። እንዲሁም ለይዘቱ የተጠቆመ የዕድሜ ክልልም ያካትታል።

  የመተግበሪያ የብስለት ደረጃን ለመረዳት የይዘት ደረጃዎቹን ይመልከቱ፣ እና ለልጅዎ ምን ትክክል እንደሆነ ለመወሰን በእነዚያ ደረጃዎች ላይ ተመስርተው ማጣሪያዎችን ያቀናብሩ። አንድ መተግበሪያ ማስታወቂያዎችን፣ የውስጠ-መተግበሪያ ግዢዎችን የያዘ ወይም የመሣሪያ ፈቃዶች የሚያስፈልገው እንደሆነ ማወቅ ከፈለጉ በመተግበሪያው የመደብር ገጹ ላይ የተጨማሪ መረጃ ክፍሉን መመልከት ይችላሉ።

 • Google ረዳትን በመጠቀም ከቤተሰብዎ ጋር የሚደሰቱባቸውን ተሞክሮዎች ያግኙ

  የእርስዎ ረዳት መላውን ቤተሰብ የሚያዝናኑ እንቅስቃሴዎች አሉት – በምሽት የቤተሰብ ጨዋታ ከማገዝ ጀምሮ እስከ ሙዚቃዊ ወንበሮች ማጫወት ድረስ። በአሁኑ ጊዜ በረዳት ለቤተሰቦች ፕሮግራም ውስጥ ከ50 በላይ ጨዋታዎች፣ እንቅስቃሴዎች እና ታሪኮች አሉ። የአንዳንዱ እንቅስቃሴ በእምነት እና ጥንቃቄ ቡድናችን ተገምግሞ የጸደቀ ነው፣ ስለዚህ ለቤተሰብ ተስማሚ እንደሆነ ያውቃሉ።

የቤተሰብዎ የመስመር ላይ ተሞክሮን የሚያቀናብሩባቸው መሣሪያዎችን ለእርስዎ መስጠት

 • በSafeSearch ማጣሪያዎች አማካኝነት በGoogle ፍለጋ ላይ ግልጽ ጣቢያዎችን ያግዱ

  የSafeSearch ቅንብሩ የወሲብ ስራ እና ግልጽ ጥቃትን ለመከላከል ግልጽ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን እና ድር ጣቢያዎችን ከGoogle ፍለጋ ውጤቶች ለማገድ የተነደፈ ነው። ይሁንና፣ ፍጹም የሆነ መሣሪያ አይደለም፣ እና አሁን ግልጽነት ያላቸው ውጤቶች ሊያገኙ ይችላሉ። በእነዚህ አጋጣሚዎች ሪፖርት ሊያደርጉት ይችላሉ – እንዲህ አይነት ግብረመልስ የSafeSearch ቅንብሩ ለሁሉም ሰው የተሻለ እንዲሆን እንድናደርገው ያግዘናል።

 • በYouTube ላይ ከተገደበ ሁነታ ጋር የዐዋቂ ሰው ቪዲዮዎችን ያግዱ

  YouTube የተገደበ ሁነታ ቅንብርን በማብራት፣ የእርስዎ ጎረምሳ ልጅ እንዳይመለከት ሊፈልጉ የሚችሉትን የዐዋቂ ሰው ይዘት እንዳይታይ እንዲያደርጉ ልናግዝዎት እንችላለን። በእኛ የገምጋሚዎች ቡድን የተገደቡ የቪዲዮ ዕድሜ ገደቦች አማካኝነት ከማጣራት በተጨማሪ የእኛ በራስሰር የሚሠራ ሥርዓት እንደ የቪዲዮው ዲብውሂብ፣ አርዕስት እና በቪዲዮው ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው ቋንቋ የመሳሰሉ ምልክቶችን ይመለከታል። የተገደበ ሁነታ ሲነቃ፣ ማናቸውንም የማይፈለጉ ውይይቶችን ለማስቀረት እንዲቻል በሚመለከቷቸው ቪዲዮዎች ላይ አስተያየቶችን ለመመልከት አይችሉም።

 • በGoogle Wifi የመሣሪያ እረፍት ጊዜ መውሰጃዎችን ያቀናብሩ እና አግባብ ያልሆነ ይዘትን ያግዱ

  Google Wifi ልጆችዎ አግባብ የሆነ ይዘት እየተመለከቱ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ያግዘዎታል። መጥፎ ነገሮችን እንዲታቀቡ ለማገዝ Google Wifi በልጅዎ መሣሪያዎች ላይ እንደ የወሲብ ስራ ወይም ግልጽ ጥቃት ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ግልጽ ድር ጣቢያዎችን በራስ-ሰር የሚያግዱ የላቀ የጣቢያ ማገድን ያቀርባል። እንዲሁም እንደ የቤት ስራ ጊዜ፣ የውጭ ጊዜ ወይም የመኝታ ሰዓት ባለ አስፈላጊ ጊዜ ላይ የWi-Fi ባለበት ማቆም መርሐግብር ማቀናበርም ይችላሉ። ከGoogle Wifi ጋር የሚመጡ የመሰየሚያዎች ባህሪውን በመጠቀም እንዲያውም በአውታረ መረብዎ ላይ ላለ እያንዳንዱ መሣሪያ የተለያዩ ማጣሪያዎችን እና ባለበት ማቆሞችን መተግበር ይችላሉ።

ጥንቃቄ ያለውና ደህንነቱ ይበልጥ የተጠበቀ የመስመር ላይ መማር ለተማሪዎች እና አስተማሪዎች መስጠት

 • በG Suite for Education ውስጥ ደህንነትን መገንባት

  G Suite for Education አስተማሪዎች እና ተማሪዎች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በመሣሪያዎች ላይ መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያግዛቸዋል። በመሠረታዊ የG Suite for Education አገልግሎቶች ውስጥ ምንም ማስታወቂያዎች የሉም፣ እና ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ (K-12) ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላሉ የG Suite for Education ተጠቃሚዎች ማስታወቂያዎችን ለማነጣጠር ምንም የተጠቃሚ የግል መረጃን አንጠቀምም። እንዲሁም አስተዳዳሪዎች አግባብ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ መመሪያዎችን እንዲያዘጋጁ እና ተማሪዎች የGoogle መለያዎቻቸውን ሲጠቀሙ ለመጠበቅ የሚያግዙ መሣሪያዎችን እናቀርባለን። ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው በሚጠቀሙባቸው የG Suite for Education አገልግሎቶች ላይ በመረጃ የታገዘ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ ለማገዝ መሣሪያዎችንና መርጃዎችን ለማቅረብ ቁርጠኞች አለን።

 • Chromebooks ለትምህርት ክፍሉ አስተማማኝ መሆናቸውን ማረጋገጥ

  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በትምህርት ክፍል ውስጥ Chromebooksን – የGoogle ላፕቶፖች – ይጠቀማሉ። አስተዳዳሪዎች ትምህርት ቤቱ በመረጠው መሠረት ለተማሪዎች ትልቅ ወይም ትንሽ ተግባራት ወይም መዳረሻ እንዲሰጧቸው የቡድን ቅንብሮችን እንዲያቀናብሩ እናስችላቸዋለን። የእኛ የግላዊነት እና የደህንነት ባህሪያት ላለፉት አራት ዓመታት የልጆች የግል ውሂብ እንደተጠበቀ እና Chromebooks በአሜሪካ የኬ-12 ትምህርት ቤቶችና በሌሎች አገሮች ባሉ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ተመራጭነት እንዲኖረው አግዘዋል።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።