በመላው በይነመረብ ላይ ደህንነትን ለማጠናከር መተባበር

Google የደህንነት ግኝቶቻችን፣ ልምዶቻችን እና ቴክኖሎጂዎቻችን በመላው ዓለም ላሉ አጋሮች፣ ተፎካካሪዎች እና ድርጅቶች የማጋራት ረጅም ታሪክ አለው። የደህንነት ስጋቶች መልካቸውን እየተቀየሩ ሲመጡ ተጠቃሚዎችን ለመጠበቅ እና አብረን ደህንነቱ ይበልጥ የተጠበቀ በይነመረብ እንድንፈጥር ለማገዝ ይህ ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪ-ደረጃ ትብብር ወሳኝ ነው።

አብረን የበይነመረቡ ደህንነት ይበልጥ የተሻለ ለማድረግ የደህንነት መፍትሔዎቻችን ማጋራት

 • ከጥንቃቄ አሰሳ ጋር ከአደገኛ ጣቢያዎች፣ መተግበሪያዎች፣ እና ማስታወቂያዎች እርስዎን መጠበቅ

  የእኛን ጥንቃቄ አሰሳ ቴክኖሎጂ አደገኛ የድርጣቢያዎችን ለመጎብኘት ሲሞክሩ በማንቃት የድር ተጠቃሚዎችን ከማልዌር እና ከአስጋሪ መልእክቶች ለመጠበቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው። ጥንቃቄ አሰሳ ከChrome ተጠቃሚዎችም ብቻ በላይ – በይነመረቡ ለሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ይህ ቴክኖሎጂያችን Apple Safariን እና Mozilla Firefoxን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶች በምርታቸው ውስጥ እንዲጠቀሙበት በነጻ ያቀርባል። ዛሬ፣ ከ3 ቢሊዮን መሣሪያዎች በላይ በጥንቃቄ አሰሳ ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በተጨማሪም የድር ጣቢያ ባለቤቶች ጣቢያዎቻቸው የደህንነት ግድፈቶች ሲኖርባቸው እናነቃቸዋለን፣ እንዲሁም ችግሮቹን በፍጥነት እንዲያስተካሉ የሚያግዟቸውን መሣሪያዎች በነጻ እናቀርባለን።

 • HTTPS ምሥጠራ በይነመረቡን በሚያስሱበት ጊዜ ደህንነትዎ እንደተጠበቀ ያቆይዎታል

  የእኛን አገልግሎቶች ከHTTPS ምሥጠራ ጋር በምትኬ ማስቀመጥ ወደ ጣቢያዎች እርስዎ ማገናኘት እና እንደ ክሬዲት ካርድ ቁጥሮች የመሳሰሉ የግል መረጃዎችን ማንም ሰው በእርስዎ መረጃ ላይ ጣልቃ ሳይገባ ማስገባት እንደሚችሉ ያረጋግጣል። ሌሎች የድር ጣቢያዎች ይህንን የታከለ ደህንነት ከእነርሱ አሠራር ጋር እንዲያጣጥሙት ለማበረታታት ሲባል ለገንቢዎች መሣሪያዎችን እና ግብዓቶችን እናቀርባለን። HTTPS ምሥጠራ የGoogle ፍለጋ ስልተ-ቀመር በእኛ የፍለጋ ውጤቶች ላይ የድር ጣቢያዎችን ደረጃ በሚሰጥበት ጊዜ የሚጠቀምበት መስፈርት ነው። በተጨማሪ እንደ .google ወይም .app ለመሳሰሉ HSTS preloading የሚጠቀሙ በእነዚህ ጎራዎች ላይ የHTTPS መጠቀምን ለሚያስፈጽሙ ከፍተኛ ደረጃ ጎራዎች ጥቅም ላይ ይውላል።

 • የደህንነት ስጋቶችን መከላከል ላይ ማገዝ እንዲችሉ ለገንቢዎች የደህንነት መጠበቂያ መሣሪያዎችን እንዲገኙ ማድረግ

  የደህንነት ቴክኖሎጂያችን ለሌሎች ዋጋ ይኖረዋል ብለን ስናምን እናጋራዋለን። ለምሳሌ፣ ገንቢዎች የድር መተግበሪያዎቻቸው በApp Engine ውስጥ የደህንነት ተጋላጭነቶች ካላቸው መፈተሽ እንዲችሉ Google የደመና ደህንነት ቃኚ በነጻ የሚገኝ እናደርግላቸዋለን።

 • Project Shield እንዳይዘጉ የዜና የድር ጣቢያዎችን ይከላከላል

  Project Shield ዜናን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ እና የምርጫ ጣቢያዎችን ከተረበሸ የአገልግሎት ክልከላ (DDoS) ጥቃቶች ለመከላከል የሚያግዝን የእኛን ቴክኖሎጂ የሚጠቀም አገልግሎት ነው። እነዚህ ጥቃቶች የድር ጣቢያዎችን ለማውረድና እንዳይሠሩ ለማድረግ እንዲሁም የሐሰት ትራፊክ እንዲንጋጋባቸው በማድረግ ድምፅ ሰጪዎች ወሳኝነት ያለውን መረጃ እንዳይደርሱ ለመከላከል የሚደረጉ ሙከራዎች ናቸው። የድርጣቢያው መጠን ወይም የጥቃቱ መጠን ምንም ይሁን ምን Project Shield ሁልጊዜ ነጻ ነው።

ኢንዱስትሪ-መር የደህንነት ፈጠራ እና ግልጽነት

 • ዒላማ ከሚደረጉ ጥቃቶች በአደጋ ላይ ያሉ ተጠቃሚዎችን ደህንነት መጠበቅ በእኛ በጣም ጠንካራው የደህንነት መጠበቂያ መጠበቅ

  ሌላው ሳይቀር ስለደህንነት ጥበቃ አስፈላጊነት በደንብ የሚረዱ ተጠቃሚዎች በአስጋሪ ተንኮሎች ወይም ሌላ የረቀቁ እና በከፍተኛ ደረጃ ዒላማ የተደረጉ ጥቃቶች ሊታለሉ ይችላሉ። የላቀ ጥበቃ ፕሮግራም እንደ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የዘመቻ ቡድኖች፣ ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ የንግድ ተቋማት መሪዎች፣ ወይም ሌላ ማንም ለተራቀቁ ዲጂታላዊ ጥቃቶች ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለሚያምኑ ማናቸውም ሰዎች ለመሳሰሉ – ዒላማ ለሚደረጉ ጥቃቶች ስጋት ያለባቸውን አካላት የGoogle መለያዎች ደህንነት ለመጠበቅ ዲዛይን የተደረገ በጣም ጠንካራው ደህንነትን የሚጠብቅ የGoogle የደህንነት መጠበቂያ ነው።

 • ደህንነቱ ይበልጥ አስተማማኝ የሆነ በይነመረብን ለማጎልበት የእኛን የአሠራር ልምዶችን ውሂብ ማጋራት

  ከ2010 ጀምሮ እንደ የቅጂ መብት ማስወገዶች፣ መንግሥት እንዲሰጠው የሚጠይቀው የተጠቃሚ ውሂብ ጥያቄዎች እና እንደ የጥንቃቄ አሰሳ ያሉ ስታቲስቲክስን ለይተው የሚያቀርብ የግልጽነት ሪፖርት አትመናል። በተጨማሪም፣ ኢንዱስትሪው የድር ጣቢያዎች እና የኢሜይል ምሥጠራ አቀባበሉ ላይ ውሂብ እናጋራለን። ይህን የምናደርገው ግስጋሴያችን ለተጠቃሚዎቻችን ለማጋራታ ብቻ ሳይሆን ደህንነቱ ይበልጥ ለተጠበቀ በይነመረብ ለሁሉም ሰው ለማኖር ሲባል ሌሎች ይበልጥ ጠንካራ የደህንነት መስፈርቶችን እንዲቀበሉ ለማበረታታት ነው።

በመላው ኢንዱስትሪ ላይ የደህንነት ደረጃን ለማላቅ መስፈርቶችን ማሻሻል

 • የደህንነት ተጋላጭነቶችን ለማጋለጥ የደህንነት ሽልማቶችን መፍጠር

  በGoogle ዘንድ፣ የግል ተመራማሪዎችን በእኛ አገልግሎቶች ውስጥ ተጋላጭነቶችን በማግኘታቸው የሚሸልሙ የተጋላጭነት አግኚዎች ሽልማት ፕሮግራሞችን በማስጀመር ረገድ ፋና ወጊዎች ነን። የእኛን ተጠቃሚዎች ደህንነታቸው እንደተጠበቁ ለማቆየት የሚያግዙ ልዩ ውጫዊ አስተዋጽዖዎችን በሙሉ ለመሸለም፣ በየዓመቱ በምርምር የገንዘብ ስጦታዎች እና የሳንካ ጥገና ሽልማቶች ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን በሽልማት እንሰጣለን። አሁን ላይ Chrome እና Androidን ጨምሮ በበርካታ የእኛ ምርቶች ላይ የተጋላጭነት ሽልማቶችን እናቀርባለን።

  በግል የሚንቀሳቀሱ ተመራማሪዎችን ከማሳተፍ ባሻገር፣ በመላው በይነመረብ ዙሪያ ጥቅም ላይ በዋለ ሶፍትዌር ላይ ያሉ የደህንነት እንከኖችን ዱካ የሚከታተል እና ለችግሮቹ መፍትሔ የሚሰጥ Project Zero የሚባል መሐንዲሶችን የያዘ የውስጥ ቡድን በተጨማሪ አለን።

 • የደህንነት መፍትሔዎችን ለማላቅ ከከፍተኛ ተመራማሪዎች ጋር መተባበር

  የእኛ ተመራማሪዎች ከምሁራን፣ ከኢንዱስትሪ ቡድኖች እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) አጋሮች ጋር የደህንነት፣ የግላዊነት፣ እና ፀረ-አላግባብ መጠቀም ምርምርን ለማላቅ በትብብር ይሠራሉ። ንቁ በሆኑ የትብብር ሥራዎች በኩል በየትኛውም ቦታ ላይ ተጠቃሚዎችን ለመጠበቅ ተሸጋጋሪ መፍትሔዎችን በማጎልበት ላይ ነን እንዲሁም የእኛ ተመራማሪዎች የእነርሱን ልዩ ተሞክሮ በማበደር ከፍተኛ ዓላማ ያላቸውን እና ለGoogle መርጃዎች መዳረሻ ለሚሰጡ የምርምር ተነሳሽነቶችን ይደግፋሉ።

 • የእርስዎን በመለያ መግባት በተቻለ መጠን ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ አድርጎ ለማቆየት የማረጋገጫ መስፈርቶችን ደረጃ ከፍ በማድረግ

  በድር ላይ ሊኖር የሚችለውን በጣም ጠንካራውን በመለያ መግቢያ እና ማረጋገጫ መለኪያ መመዘኛዎች በጋራ-በመፍጠር ወይም ለእኛ እንደሚስማሙ አድርጎ አጣጥሞ በመቀበል ምንጊዜም ከማንም ይልቅ ከፊት መሥመር ላይ ነን። በመላው እንዱስትሪው ከሌሎች ጋር በትብብር እንሠራለን እንዲሁም ማዕከላዊነት የተላበሱ የድር መለኪያ መመዘኛዎችን በማጎልበት ቴክኖሎጂ እናጋራለን። እንዲህ ካሉት ለትርፍ ካልቆሙ ድርጅቶች ጋር ከሚደረጉ አጋርነቶች መካከል አንዱ የሆነው FIDO Alliance ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው ደህንነቱ የተጠበቀ የመለያ መዳረሻ መኖሩን በማረጋገጥ መጠቀም እንዲችሉ አዲስ የኢንዱስትሪ መለኪያ መመዘኛዎችን ለማቀናበር እና ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ ሠርቷል።

 • ለሁሉም የተሻለ ደህንነትን ለማምጣት የቤት ለቤት ስምሪት ኣና የመስመር ላይ ደህንነት ጥበቃን ማቅረብ

  በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች በመስመር ላይ እንዴት ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ለመቆየት እንደሚችሉ እንዲረዱ ለማገዝ የትምህርት ማቴሪያሎችን፣ ሥልጠናዎችን እና መሣሪያዎች እናቀርባለን። የእኛ የቤት ለቤት ስምሪት ቡድን በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ሰዎችን – መምህራንን፣ ተማሪዎችን፣ ወላጆችን፣ የዕድሜ አንጋፋዎችን፣ እንዲሁም የአካል ጉዳት ያለባቸውን ጨምሮ – ከመስመር ላይ ደህንነት ግብዓቶች እና ሥልጠናዎች ጋር ይደርስባቸዋል።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።