በኢንዱስትሪ መር ደህንነት አማካኝነት መስመር ላይ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የምንሰራው ነገር ሁሉ እንደ አይፈለጌ መልዕክት፣ ተንኮል አዘል ዌር እና ቫይረሶች ያሉ ስጋቶችን ለማግኘት እና ለማገድ በሚያግዙ ኃይለኛ አብሮገነብ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ጥበቃ የሚደረግለት ነው። እነዚህን የደህንነት ቴክኖሎጂዎች ለአጋሮች እና ተፎካካሪዎች እናጋራለን፣ ይህም ሁሉም ሰው መስመር ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ እንዲቆይ የሚያግዙ የኢንዱስትሪውን መስፈርቶች ከፍ ያደርጋሉ።

አብሮገነብ ጥበቃ

በምንሰራው እያንዳንዱ ነገር ውስጥ ጥበቃን መገንባት

የGoogle አገልግሎቶች በዓለም ካሉ የላቁ የደህንነት መሠረተ-ልማቶች ውስጥ በአንዱ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይጠበቃሉ። ይህ አብሮገነብ ደህንነት የመስመር ላይ ስጋቶችን አግኝቶ ይከላከላል፣ በዚህም እርስዎ የግል መረጃዎ ደህንነት የተጠበቀ መሆኑ መተማመን ይችላሉ።

የበለጠ ለመረዳት

የደህነት አመራር

በመላው በይነመረብ ላይ ደህንነትን ለማጠናከር መተባበር

Google የደህንነት ግኝቶቻችን፣ ልምዶቻችን እና ቴክኖሎጂዎቻችን በመላው ዓለም ላሉ አጋሮች፣ ተፎካካሪዎች እና ድርጅቶች የማጋራት ረጅም ታሪክ አለው። የደህንነት ስጋቶች መልካቸውን እየተቀየሩ ሲመጡ ተጠቃሚዎችን ለመጠበቅ እና አብረን ደህንነቱ ይበልጥ የተጠበቀ በይነመረብ እንድንፈጥር ለማገዝ ይህ ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪ-ደረጃ ትብብር ወሳኝ ነው።

የበለጠ ለመረዳት

የደህንነት ጠቃሚ ምክሮች

ደህንነትዎን መስመር ላይ ይበልጥ የተጠበቀ እንዲያደርጉ የሚያግዙ ጠቃሚ ምክሮች

ይበልጥ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን እንዲፈጥሩ፣ መሣሪያዎችዎን እንዲጠብቁ፣ የማስገር ሙከራዎችን ለመከላከል እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በይነመረቡን እንዲያስሱ አንዳንድ ፈጣን ጠቃሚ ምክሮችን እና ምርጥ ልምዶችን አሰባስበናል።

የበለጠ ለመረዳት

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።