ልጆች ብልህ እና በራሳቸው የሚተማመኑ የመስመር ላይ ዓለም አሳሽ እንዲሆኑ ማገዝ

Google ልጆች መስመር ላይ የተሻሉ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ ለማስተማር ብልህ፣ የሰለጠኑ ዲጂታል ዜጋዎች እንዲሆኑ ለማገዝ መርጃዎችን እና ጠቃሚ ምክሮችን ፈጥረናል።

በእነዚህ ጠቃሚ ምክሮች እና መርጃዎች አማካኝነት መስመር ላይ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫዎችን ያድርጉ

 • ልጆች በBe Internet Awesome አማካኝነት ብልህ ዲጂታል ዜጋዎች እንዲሆኑ ማገዝ

  ከበይነመረቡ ምርጡን ለማግኘት ልጆች በመረጃ የታገዙ ውሳኔዎችን ለማድረግ መዘጋጀት አለባቸው። ይህ ፕሮግራም ልጆች የመስመር ላይ ዓለምን በራሳቸው በመተማመን እንዲያስሱ የዲጂታል ዜግነት እና ጥንቃቄ መሠረታዊ ነገሮችን ያስተምራቸዋል። በአራት ፈታኝ ጨዋታዎች ቁልፍ የዲጂታል ደህንነት ትምህርቶችን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር በሚሰጠው የመስመር ላይ የጅብድ ጨዋታ በሆነው Interland አማካኝነት ልጆች እየተጫወቱ ምርጥ የበይነመረብ ተሞክሮ ልምድ ይችላል።

  እስካሁን ድረስ ይህን ፕሮግራም በአሜሪካ እና ላቲን አሜሪካ ውስጥ ነው የለቀቅነው፣ እና ወደ ተጨማሪ ገበያዎች የመልቀቅ ዕቅዶች አሉን። እንደ የመስመር ላይ ጥንቃቄ ትዕይንት አካል ታዳጊዎች እንዴት መስመር ላይ ብልጥ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ለማገዝ ይህን ስርዓተ-ትምህርት በቀጥታ በአሜሪካ ውስጥ ወዳሉ ትምህርት ቤቶች ወስደናል።

በጥንቃቄ ያጋሩ

መልካም (እና መጥፎ) ዜና መስመር ላይ በፍጥነት ነው የሚዛመተው፣ እና ልጆችና ታዳጊዎች ካላስተዋሉ ራሳቸው ዘላቂ በሆኑ ችግሮች ውስጥ ሊያገኙ ይችላሉ። እንዴት አግባብ በሆነ መልኩ ለትክክለኛዎቹ ሰዎች ማጋራት እንደሚችሉ የሚያውቁባቸው ጠቃሚ ምክሮችን ፈጥረናል።

 • ስለዲጂታል አሻራቸው ያስተምሯቸው

  ከልጆችዎ ጋር አብረው በመሆን ለራስዎ ወይም ልጆችዎ ለሚወዱት ሙዚቀኛ መስመር ላይ ፈልጉ፣ እና ስለሚያገኙት ነገር ይነጋገሩ። አስቀድመው ውጤቶቹን መመልከት ሳይሻልዎት አይቀርም። ሌሎች ከእነዚህ ውጤቶች ስለእናንተ ምን ማወቅ እንደሚችሉ እና እንዴት መስመር ላይ የዲጂታል አሻራ እንደምታዳብሩ ይነጋገሩ።

 • ማህበራዊ ፉክክርን ለመቀነስ ያግዙ

  ልጅዎ ጓደኛዎች መስመር ላይ የሚያጋሩት ነገር የአጠቃላዩ ጉዳይ ቁንጽል እንደሆነ ይህም አብዛኛው ጊዜ ድምቀቶቹን እንደሆነ ማወቃቸውን ያረጋግጡ። ሁሉም ሰው የማያጋራውን ደባሪ፣ አሳዛኝ ወይም አሳፋሪ አፍታዎች እንዳለው ያስታውሷቸው።

 • ምን እንደሚጋራ ላይ የቤተሰብ ህጎችን ይፍጠሩ

  እንደ ፎቶዎች ወይም የግል መረጃ ያለ መስመር ላይ መጋራት የሌለባቸው ነገሮች በግልጽ ለቤተሰብዎ ይንገሩ። ጥቂት ፎቶዎችን አብረው ይነሱና ኃላፊነት በሚሰማው መልኩ ማጋራት ምን እንደሚመስል ላይ ይነጋገሩ። ለምሳሌ፣ ልጅዎ የራሳቸው ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ፎቶዎች ከማጋራታቸው በፊት እንዲያስቡ ያበረታቷቸው። እርግጠኛ ካልሆኑ ፈቃድ እንዲጠይቁ ያስታውሷቸው።

 • ከልክ በላይ ስለማጋራት ያስተምሯቸው

  እንደ የተጋራውን ነገር ማውረድ ወይም የግላዊነት ቅንብሮችን ማስተካከል ያሉ ከልክ በላይ ለሆነ ማጋራት መፍትሔዎችን ያሰላስሉ። ከተከሰተ ነገሮችን እያገናዘቡ ይሂዱ። አንዳንድ አሳፋሪ አፍታዎች በጣም ከባድ ናቸው፣ ነገር ግን ሌሎቹ ዝም ብለው ጥሩ የመማሪያ አጋጣሚዎች ናቸው።

በሐሰተኛው እንዳይታለሉ

ልጆችዎ መስመር ላይ የሚያጋጥሟቸው ሰዎች እና ሁኔታዎች ሁልጊዜ መስለው እንደቀረቡት አለመሆናቸውን እንዲረዱ ማገዝ አለብዎት። እርስዎ ልጆች እንዴት እውነተኛውንና ሐሰተኛውን ነገር መለየት እንደሚችሉ እንዲረዱ ማገዝ ላይ ጠቃሚ መመሪያ ገንብተናል።

 • የማስመሰል ወንጀል ያስረዱ

  ለምን የሆነ ሰው የይለፍ ቃላቸውን ወይም የግል ውሂባቸውን ማግኘት ሊፈልግ እንደሚችል ያስረዷቸው። በዚህ መረጃ አማካኝነት የሆነ ሰው መለያቸውን ሊጠቀም እና እነሱን ሊያስመስል ይችላል።

 • የማሥገር ሙከራዎችን እንዲለዩ ያግዟቸው

  የእርስዎ ልጆች ሰዎች የግል መረጃቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ ለማታለል እየሞከሩ እንደሆኑ ላያውቁ ይችላሉ። ከባዳ የመጣ፣ የመለያ መረጃን የሚጠይቅ ወይም ግራ የሚያጋባ የሚመስል ዓባሪ ያለው መልዕክት ሲያገኙ ወደ እርስዎ እንዲመጡ ያስተምሯቸው።

 • ማጭበርበሮችን እንዲያውቁ ያስተምሯቸው

  ልጆችዎ አንዳንድ የሚመስል አታላይ ማጭበርበሮች ከጓደኛ የመጣ እንደሚመስሉ ያሳውቋቸው። ጎበዝ አዋቂዎችም ይሸወዳሉ! መልዕክቱ ወጣ ያለ ከመሰለ እርስዎ ጋር እንዲመጡ ያድርጓቸው። ለስጋታቸው ምላሽ መስጠት እምነትን መገንባት ላይ ከባድ አስተዋጽዖ አለው።

 • አብራችሁ የደህንነት ምልክቶችን ፈልጉ

  አንድ ድር ጣቢያን አብራችሁ ጎብኙና የደህንነት ምልክቶችን ፈልጉ። ዩአርኤሉ ከጎኑ በደህንነት የተጠበቀ መሆኑን የሚያሳይ የቁልፍ ጋን ምልክት አለው ወይም በhttps ይጀምራል? ዩአርኤሉ ከጣቢያው ስም ጋር ይዛመዳል? አንድ ጣቢያ ጋር ሲደርሱ ማስተዋል ያለባቸውን ምልክቶች እንዲያገኙ ያግዟቸው።

የምሥጢሮችዎን ደህንነት ይጠብቁ

የግል ግላዊነት እና ደህንነት ልክ ከመስመር ውጭ እንደሆኑት ሁሉ መስመር ላይም አስፈላጊ ናቸው። ልጆችዎ የእነሱ መሣሪያዎች፣ ዝና እና ግንኙነቶች እንዳይጎዳ ለመከላከል እንዴት ውዱ መረጃቸውን መጠበቅ እንደሚችሉ መረዳት አለባቸው።

 • ለመስበር አስቸጋሪ የሆኑ የይለፍ ቃላትን ይፍጠሩ

  አንድን የማይረሳ ሐረግ ወደ ጠንካራ የይለፍ ቃል እንዴት እንደሚቀይሩ ያስተምሯቸው። ቢያንስ ስምነት የተቀላቀሉ የጉዳይ ፊደላትን ይጠቀሙ እና አንዳንዶቹን ወደ ምልክቶች እና ቁጥሮች ይለውጧቸው። ለምሳሌ «My younger sister is named Ann» የሚለው myL$1Nan ይሆናል። የራስን አድራሻ፣ የልደት ቀንን፣ 123456 ወይም «password» የመሳሰለ ደካማ የይለፍ ቃልን መጠቀም ሌላ ሰው በቀላሉ ሊገምታቸው መቻሉን እንዲገነዘቡ ያግዟቸው።

 • የግል መረጃቸው የግል እንደሆነ ያቆዩት

  ምን የግል መረጃ – እንደ የቤት አድራሻዎቾቻቸው፣ የይለፍ ቃላታቸው ወይም የሚሄዱበት ትምህርት ቤት ያለ – የግል እንደሆነ ማቆየት እንዳለባቸው ያናግሯቸው። እንዲህ ያለ መረጃ ከተጠየቁ ወደ እርስዎ እንዲመጡ ያበረታቷቸው።

 • ጥሩ የይለፍ ቃል ንጽሕናን ያስተምሩ

  የእነሱን የይለፍ ቃል የትም ሌላ ቦታ ከማስገባታቸው በፊት ዳግም እንዲያስቡበት እና ትክክለኛው መተግበሪያ ወይም ጣቢያ መሆኑን ዳግም እንዲያረጋግጡ ያስተምሯቸው። ሲጠራጠሩ ምንም ነገር ከማስገባታቸው በፊት ወደ እርስዎ በመምጣት እርስዎን ማነጋገር አለባቸው። በተጨማሪ፣ ለተለያዩ መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች የተለያዩ የይለፍ ቃሎች እንዲኖራቸው እንዲያደርጉ ያበረታቷቸው። ለእያንዳንዱ መተግበሪያ ጥቂት ፊደላትን የሚያክሉበትን አንድ ዋና የይለፍ ቃል ሊኖራቸው ይችላል።

 • ቀልድ እንዳይቀለድባቸው ለመከላከል ያግዟቸው

  የይለፍ ቃላቸውን የግል እንደሆነ በማስቀመጥ ሌሎች ሰዎች መለያዎቻቸውን ደርሰው የሐሰት ወይም አሳፋሪ መልዕክቶችን እንዳይልኩ ለመከላከል ማገዝ እንደሚችሉ ያስታውሷቸው።

ደግ መሆን አሪፍ ነው

በይነመረቡ አዎንታዊነትን ወይም አሉታዊነትን ለማሰራጨት ጥቅምላይ መዋል የሚችል ኃይለኛ አጋጋይ ነው። ልጆች መስመር ላይ በሚያደርጉት ድርጊቶች ላይ «እርስዎ ላይ እንዲደረግ የሚፈልጉትን ነገር በሌሎች ላይ ያድርጉ» የሚለውን ፅንሰ-ሐሳብ በመተግበር ክብር ባለው መልኩ አጸፋ እንዲሰጡ ያግዟቸው፣ በዚህም ለሌሎች አዎንታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ እና የጉልበተኝነት ባህሪን ያሰናክላሉ።

 • የመስመር ላይ ጉልበተኝነትን በተመለከተ ውይይት ይፍጠሩ

  ስለትንኮሳ ወይም ሰዎች ሁን ብለው ሌሎች ለመጉዳት ብለው የመስመር ላይ መሣሪያዎችን ስለተጠቀሙባቸው ጊዜያት ይነጋገሩ። ልጆችዎ ይህን ካዩ ወይም ካጋጠማቸው ማን ጋር እንደሚሄዱ ያቅዱ። እነሱ ወይም ጓደኛዎቻቸው የመስመር ላይ ክፋት አጋጥሟቸው ከሆነ ይጠይቋቸው። አንዳንድ ሊጠይቋቸው የሚችሏቸው ጥያቄዎች፦ በምን አይነት መልኩ ነው የተከናወነው? ምን ተሰማህ/ሽ? ምናልባት ለሆነ ሰው ስለአንድ መጥፎ አስተያየት በመንገር ለማስቆም ማገዝ እችላለሁ ብለህ/ሽ አስበሃል/ሻል?

 • የቤተሰብዎን እሴቶች መስመር ላይ ይመስርቱ

  መስመር ላይ ከእነሱ ምን አይነት ባህሪ እንደሚጠብቁ በግልጽ ይንገሯቸው። ሌሎች እንዲያዙ በሚፈልጉበት መንገድ መያዝ እና ፊት ለፊት ሲሆኑ የሚናገሩትን ነገር ብቻ መስመር ላይ መናገር ጥሩ ጅምሮች ናቸው።

 • አንድ ሰው ከተናገረው ነገር በስተጀርባ ስላለው ትርጉም ይነጋገሩ እና አዎንታዊነትን ያበረታቱ

  ስለአነጋገር ስሜት ይነጋገሩ እና አንድ ሰው መስመር ላይ ለተናገረው ነገር የተሳሳተ ትርጉም መስጠት ቀላል እንደሆነ ልጆችዎን ያስታውሷቸው። በጎ ሐሳብ እንደሆነ አድርገው እንዲገምቱና አንድ ሰው የተናገረው ነገር ካልተረዱ ጓደኛዎቻቸውን እንዲጠይቁ ያበረታቷቸው። መስመር ላይ አዎንታዊ መልዕክቶችን መላክ እና መቀበል እንዴት ጥሩ ስሜት እንዳለው ይነጋገሩ። አዎንታዊ አስተያየት ወይም መልዕክት ለመላክ አንዱን መተግበሪያዎ መጠቀሙን ያስቡበት።

ሲጠራጠሩ ይነጋገሩበት

በሁሉም የዲጂታል አይነት ግንኙነቶች ላይ መተግበር ያለብዎት ዕውቀት፦ ልጅዎ የሆነ አጠራጣሪ ነገር ሲገጥማቸው አንድ የሚታመን አዋቂ ማናገር የሚችሉ እንደሆኑ ሊሰማቸው ይገባል። ቤት ውስጥ ግልጽ ንግግርን በማበረታታት ይህን ባህሪ መደገፍ ይችላሉ።

 • መስመር ላይ ምን እንደሚያደርጉ ይነጋገሩ

  ጊዜ ወስደው ቤተሰብዎ ቴክኖሎጂን እንዴት እንደሚጠቀም ላይ ይነጋገሩ። ልጅዎ በብዛት በሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች ላይ ፍላጎት ያሳዩና እንዲያስጎበኙዎት ይጠይቋቸው። መተግበሪያዎቻቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው እና ስለእነሱ የሚወዷቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ይወቁ።

 • በጊዜ ሂደት ላይ ሊቀየሩ የሚችሉ ገደቦችን ያቀናብሩ

  እንደ የይዘት ማጣሪያዎች እና የጊዜ ገደቦች ያሉ ደንቦች ለልጆችዎ መለያዎች ያቀናብሩ፣ እና ልጆችዎ ዕድሜያቸው እያደገ ሲሄድ እነዚህ ደንቦች ሊቀየሩ እንደሚችሉ ያሳውቋቸው። ቅንብሮች በጊዜ ሂደት ላይ ለውጥ ማሳየት አለባቸው። እንዲሁም ዝም ብለው «አቀናብረው አይርሱት»።

 • ሊሄዱባቸው የሚችሉባቸው ሰዎችን እንዲለዩ ያግዙ

  በመስመር ላይ የሚያስጨንቃቸው ነገሮችን በሚያገናኙበት ጊዜ ሊሄዱባቸድው የሚችሏቸው ሦስት ታማኝ ሰዎችን ይለዩ። የታመነ ሰው ባዩት ነገር ላይ እንዲያጽናኗቸውና ለወደፊቱ እንዲህ ያለ ነገር እንዳያዩ ለመከላከል ያግዛሉ።

 • መስመር ላይ የጥራት ጊዜን ይደግፉ

  ፈጠራን ወይም የችግር አፈታት ክኅሎቶችን በሚያስተምሯቸው ጨዋታዎች እና መተግበሪያዎች ላይ ጊዜያቸውን እንዲያጠፉ ያበረታቷቸው።

ስለ የደህንነት ጥረቶች የበለጠ ይረዱ

የእርስዎ ደህንነት

ከኢንዱስትሪ መር ደህንነት ጋር መስመር ላይ ለእርስዎ ጥበቃ እናደርግልዎታለን።

የእርስዎ ግላዊነት

ለሁሉም ሰው የሚሠራ ግላዊነትን ገንብተናል።

ለቤተሰቦች

ለእርስዎ ቤተሰብ መስመር ላይ ምን ትክክለኛ እንደሆነ እንዲያስተዳድሩ እናግዝዎታለን።